ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ

ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ  በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።

ህብረቱ ዶክተር አርከበ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ ማቅረቡን  ነው በመግለጫው ያመለከተው።

የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ በየካቲት 24 እና 25 2013 ባደረገበት ወቅት  ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ወክለው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።

ዶክተር አርከበ ባለፉት ሰላሳ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ ህብረቱ  ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply