ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የህንድ የባህል ግንኙነት ካውንስል (ICCR) የክብር አልሙናይ ሽልማትን ተቀበሉ

ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የህንድ የባህል ግንኙነት ካውንስል (ICCR) የክብር አልሙናይ ሽልማትን በህንድ አገር ኒውዴልሂ ከተማ ከሚገኘው ዴልሂ ዩኒቨርስቲ ተቀብልዋል፡፡

ሚኒስትሯ ሽልማቱን ያገኙት ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር ያላትን የላቀ የባህል ትስስር፣ ወዳጅነትና የበጎ ሥራ ተግባራት እንዲዳብር በማድረጋቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡

በተጨመሪም ዶ/ር ኤርጎጌ ለዚህ ሽልማት የተመረጡት፤ በኢትዮጵያ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ ከሥርዓተ-ፆታ ስትራቴጂ፣ ከሥነ ተዋልዶ ጤና ስትራቴጂዎች እና ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ ፖሊሲዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ባደረጉት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም እ.አ.አ በ2019 በአዲስ አበባ ከ500 ለሚበልጡ አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ አገልግሎት ህንድ አገር ከሚገኘው BMVSS ድርጅት እንዲያገኙ በአበረከቱት አስተዋጽኦ መሰረት ለዚህ ሽልማት መታጨታቸው ተነግሯል፡፡

በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በኤምባሲው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የህንድ መንግስት ተወካዮች እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ተገኘተዋል፡፡

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የ ICCR በቸኛዋ አፍሪካዊ ተሸላሚ መሆናቸውንም ህንድ ኒውዴልሂ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው የህንድ ኤምባሲና ከህንድ የባህል ግንኙነት ካውንስል (ICCR ) ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply