You are currently viewing ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባልነታቸው ተነሱ – BBC News አማርኛ

ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባልነታቸው ተነሱ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/11B43/production/_121851527_8a1e9bc5-9977-4d64-9c2f-866974469384.jpg

ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ከዛሬ ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነታቸው መነሳታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Tesfa

    ዛሬም ትላንትናም ሃገራችን የሚያተራምሷት ፊደል ቆጥረናል፤ ተምረናል እኛ የምንላችሁን ስሙ የሚሉ እቡይ ምሁራን ናቸው። ዶ/ር እሌኒ በዙም በተደረገው ስብሰባ ላይ ጥሪውን ተቀብላ ሰልፈኛ ከመሆኗ በፊት ሊያስከትል የምችለውን ፓለቲካዊና ህብረተሰባዊ ጫና መመዘን ነበረባት። ያው እዪኝና እወቁኝ፤ ውደድኝ እና ንገሩልኝ በሚለው በዚህ ንፉዝ አለም ውስጥ ነገርን ማመዛዘን ከቀረ ቆይቷል። አፍ እንዳመጣ ተናገሮ፤ እግርና ተሽከርካሪ ባደረሰው ገብቶና መድረክ ላይ ወጥቶ አዩኝ፤ ሰሙኝ፤ የማን ወገን ናቸው፤ ዘራቸውስ ከነማን ነው ብሎ ልክ እንደ ምድር አራዊት በክልል መኮልኩሉ ኩራት የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
    ሲጀመር የፕሮግራሙ መሪ ፕ/ሩ ያልታያቸው ወይም ዘግይቶ የገባቸው ነገር ያለ ይመስላል። በቅርቡ የሰጡትን የማሰተባቢያ ሃሳብ ላዳመጠ ሰውዬው በእድሜ ከመግፋታቸው የተነሳ በቅንነት የጠሩት ስብሰባ አስመስለው አቅርበውታል። ይህን ግን ለማመን ይከብዳል። እንዴት አድርጎ በህዝብ የተመረጠን መንግስት ማውረድ እንደሚቻል የሚመክረው ይህ ስብሰባ በአሜሪካን መንግስት ድጋፍ ከሚደረገው የሽግግር መንግስት ስሌት ጋር የሚገናኝ ነው። ስብሰባው ለኢትዮጵያ መልካም በሚያስቡ ሰዎች ቅን አስተሳሰብ የተከወነ ነው ብሎ የሚያምን ማንም ሰው ቂል ነው። ከአማራ ተወካይ በስተቀር በ 9 የታክሲ ነጂ ስብስቦችና በወያኔው ደም አፍሳሽና ዘረኛ ዘራፊ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የተዋቀረው የሙታን ፓለቲከኞች ስብስብ ሃሳብና ግብ የዚሁ የዙም ስብሰባ አካል ነው። ዶ/ር እለኒ ብርሃነን ስታሞግስ ከምን ተነስታ እንደሆነ ለመረዳት ግራ ያጋባል። ይህ የወያኔ አጥፊ ሃይል የትግራይ ህዝብ ጠላት፤ ኢትዮጵያን የሸጠ የደም ሰው ለመሆኑ እልፍ መረጃ አለ። ሰው ፕ/ር፤ ዶ/ር፤ እንጅኒየር ገለ መሌ ስለተባለ ሰዋዊ እይታ ይኖረዋል ማለት አይደለም። የትግራይ እብዶች ሰው እያስጨረሱና እየጨረሱ ትግራይ ትቀድማለች ቢሉን የሚገርም አይደለም። የሚቀድሙት ከኋላ ሆነው በለውና በላት አውድም እያሉ የሚልኳቸው እንጂ እነርሱ ድሮም ሆነ አሁን ውጊያንና ሞትን አያውቋትም። እንዲህ ያለ እብደት ባለበት በነደደ እሳት ውስጥ ቁማ ነው ዶ/ር እሌኒ ኢኮኖሚውን መልሶ ስለመገንባት የምታወራው። እኛ ኮ ጥቁሮች ነን። ሁሌ የእነርሱ ለማኞች እንድንሆን ነው ነጩ ዓለም የሚፈልገው። የዓለም ባንክ (World Bank)፤ አይ ኤም ፍ (IMF) ሊያድጉ በሚታገሉ ሃገሮች ላይ የሚያደርሱት የእዳ ክምርና ልዪ ልዪ አሻጥር ይህ ነው አይባልም። የዶ/ር እሌኒ የማርሻል ፕላን ጥያቄ የቆመችበትን መሬት እንዳለማወቅ ይቆጠራል። አሜሪካ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ፍጻሜ በህዋላ ለሰው ልጆች መብትና ደህንነት ቁማ አታውቂም። ሃገርን ለመናድና ለራሷ ጥቅም እንጂ።
    ይህን የዙም ስብሰባ ያዘጋጅና የተካፈሉ ሁሉ ማድረግ የሚኖርባቸው አንድ ነገር ብቻ ነው። አዎን መስሎን ተካፍለናል፤ አጥፍተናል በማለት ህዝባችን ይቅርታ መጠየቅ ነው። ሌላው ዝባዝንኬ ነው። ቤቴ ተፈተሸ፤ አንዲት ሴት ጠቆመች፤ ለሃገር ደህነንት ነው ስብሰባው የሚባለው ጊዜ ያለፈበት መወሻከት ሁሉ ተቀባይነት የለውም። ዛሬ ሰው ነቅቷል። አምታችና አማቺን ለይቷል። የማያልቅ ሰበብ እየመዘዙ በማያቆም እግር ወገብን ይዞ መከራከሩ ትርፍ የለሽ ነው። የሃገራችን የፓለቲካ አዙሪትና የእብደት ሽክርክሪት የሚገታበትን መንገድ መፈለግ ማለፊያ ሆኖ ሳለ በለው፤ በያት፤ ያዘው፤ ጥለፈው፤ ጀጋኑ፤ መጣንባችሁ ወዘተ የሚባለው ኋላ ቀር እይታና ጠበንጃ አምላኪነት በሃገራችን ምድር እስካልቆመ ድረስ መገዳደላችን ይቀጥላል። ወንድሙንና እህቱን ገድሎ ከሚፎክር የአስተሳሰብ ጉዞ ህዝባችን የምናላቀው ተምረናል የምንለው እብደታችን በሰከነ አዕምሮ በመተካት ለሰላም የምንችለውን አስተዋጾ ማድረግ ስንችል ብቻ ነው፡፡ ባይገባን በዘር ፓለቲካ ሰክረን እንጂ በዚህ በዚያም የሚያልቀው ወገናችን ነው። አባትና ልጅ ጎራ ለይተው የሚገዳደሉበት ፊልሚያ! ዶ/ር እሌኒም በይፋ መሳተፏ ስህተት መሆኑን አምና በመቀበል ወደፊት ላይደገም ቃል ገብታ የነበራትን የህዝብ ከበሬታ እንደገና ማደስ ይኖርባታል እንጂ ተጨማሪ ጥያቄና መልስ፤ ወይም ማብራሪያ በጭራሽ አያስፈልግም። የሆነውን አይናችን አይቷል። ጆሮአችን ሰምቷል። በቃኝ!

Leave a Reply