You are currently viewing ዶ/ር ዮናስ ብሩን እንደማሳያ ፥- የአቢይ አህመድ ስትራቴጂያዊ ደጋፊዎች እና ታክቲካል ተቃዋሚዎች ሚስጢር ======= ሸንቁጥ አየለ ======= ዶ/ር ዮናስ ብሩ የአቢይ አህመድ ስትራቴክጅ…

ዶ/ር ዮናስ ብሩን እንደማሳያ ፥- የአቢይ አህመድ ስትራቴጂያዊ ደጋፊዎች እና ታክቲካል ተቃዋሚዎች ሚስጢር ======= ሸንቁጥ አየለ ======= ዶ/ር ዮናስ ብሩ የአቢይ አህመድ ስትራቴክጅ…

ዶ/ር ዮናስ ብሩን እንደማሳያ ፥- የአቢይ አህመድ ስትራቴጂያዊ ደጋፊዎች እና ታክቲካል ተቃዋሚዎች ሚስጢር ======= ሸንቁጥ አየለ ======= ዶ/ር ዮናስ ብሩ የአቢይ አህመድ ስትራቴክጅ ደጋፊ ሲሆን ሞኛሞኞችን ለማደንዘዝ ደግሞ የአቢይ አህመድ ታክቲካል ተቃዋሚ ነዉ። የአቢይ አህመድ ስትራቲጂያዊ ደጋፊዎች እና ታክቲካል ተቃዋሚዎችን በዝርዝር ከእነ ሙሉ ትንታኔዉ ማቅረብ ይቻላል።ለዛሬ አንድ ማሳያ ብቻ እናጣቅስ። ዮናስ ብሩ የአቢይ ታክቲካል ተቃዋሚ እና ስትራቴጂክ ደጋፊ መሆኑን ለማረጋገጥ ከጋዜጠኛ መአዛ ጋር ያደረገዉን ዉይይት አዳምጡት። የሰዉዬዉ ኢንተርቪዉ ሲጠቃለል ፋኖ ለምን እንደሚታገል ገና በዝርዝር አይታወቅም የሚል ነዉ። እናም ፋኖ ወደፊት ዝርዝር አላማዉን ወደፊት ጽፎ ማቅረብ አለበት ይልሃል ዮናስ ብሩ። ፋኖም ዝርዝር አላማዉን አቅርቦ ከአቢይ ጋር መወያዬት አለበት ይልሃል። ከዚያም ወደ ታክቲካል ተቃዉሞዉ ሲገባ የአቢይን መንግስት ገሰጽ ያደረገ መስሎ ከመጥፋትህ በፊት ተደራደር እንጂ የሚል ምክር ለአቢይ ይለግሳል። ወደ ዋናው ስትራቴጂያዊ ደጋፊነቱ ሲሸጋገርም ፋኖዎች በዚህ ሰኣት አቢይ ይዉረድ ፡ መንግስት ይለወጥ የሚል ጥያቄ ፈጽሞ ማንሳት የለባቸዉም ይልሃል። እንዲህ እንደ ዮናስ ብሩ ተቃዉሞ ጎራዉ ዉስጥ የሚራወጡ ተኩላዎች ስታገኝ ሁሌም አንድ ነገር አስታዉስ። የኦነግ/ኦህዴድ ታክቲካል ተቃዋሚዎች እና ስትራቴጂያዊ ደጋፊዎች መሆናቸዉን ትዝ ይበልህ። መልክና ስማቸዉም ብዙ መሆኑን አትርሳ። እስከ ሞት በሚወስድ የህዝብ ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር በታክቲካል ጉዳይ ተስማምተዉ በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ከሚለያዩህ ጋር ፈጽሞ አብረህ እንዳትርሞጠሞጥ። ከአንተ የትግል ራእይ ጋር በስትራቴጂያዊ ጉዳይ ከሚስማሙህ ጋር ሆኖም በታክቲካል/ ስልታዊ/ አካሂያድ ካንተ ጋር ለጊዜዉ ከማይስማሙት ጋር ግን አብረህ ተሰለፍ። በምሳሌ ለማሳለጥ “ኦነግ/ኦህዴድ ከ10 ሚሊዮን የሚበልጥ የአማራ ህዝብ ላይ በማፈናቀልም በመግደልም የዘር ፍጅት የፈጸመ ሀይል ነዉ።ወደፊትም የዚህ ሀይል ዋና የህይወት ዘመኑ ግብ አማራን ማጥፋት ነዉና ይሄን ሀይል ከኢትዮጵያ መንቀል አለብን።ኦነግ/ኦህዴድ በምድሪቱ እያለም ፈጽሞ የአማራ ህዝብ እንደሰዉ እንዲኖር አይፈቅድምና ከዚህ ጭራቅ ጋር መደራደር እራስን ማሞኘት ነዉ” በሚል ስትራቴጂያዊ ግብ ላይ ከምትስማማቸዉ ሀይሎች ጋር አብረህ ስራ። በታክቲካል አካሂያድ ላትስማማ ብትችልም ከላይ ባለዉ ስትራቴጂ ጉዳይ ላይ ላይ ከተስማማህ ግን አብረህ መስራት አለብህ። ታክቲካል አካሂያድ የሚባለዉም ድርጅቱን “ሀ” እንበለዉ ወይስ “ለ” እንበለዉ? በክፍለሃገር ስም እንደራጅ፡ ወይስ በሀገር አቀፍ ስም እንደራጅ የሚሉ እና የመሳሰሉ ጉዳዮች ናቸዉ። በተቃራኒዉ ግን ፋኖ አላማ የለዉም ብሎ በምላሱ ግን ፋኖን እደግፋለሁ ማለት ታክቲካል ድጋፍ ሲሆን መልሶ ደግሞ ፋኖ ዝርዝር አላማዉ አይታወቅም ማለት ደግሞ ስትራቴጂያዊ ፋኖን የመቃወም አካሂያድ ነዉ።የዮናስ ብሩን ኢንተርቪዉ አድምጠዉ። በሌላ በኩል ደግሞ አቢይ አህመድን አሁን ከስልጣን ይዉረድ ማለት የፋኖ ጥያቄ መሆን የለበትም ማለት እና የፋኖ ትግል መንግስት ለዉጥ ላይ ማተኮር የለበትም ማለት የኦነግ/ኦህዴድ ስትራቴጂያዊ ደጋፊነት ነዉ።የአቢይ መንግስት ስልጣን ላይ እያለ የአማራ ህዝብ በየትኛዉም ኢትዮጵያ መኖር እንደማይፈቀድለት እየታወቀ የአቢይ መንግስት ይቀጥል ማለት ስትራቴጂያዊ የአማራ ህዝብ ጠላትነት ነዉ።ዮናስ ብሩ ማለት በስትራቴጂያዊ መነጽር ሲቃኝ የአማራ ህዝብ ስትራቴጂያዊ ጠላት ሆኖ ሳለ ከንፈር መጠጣ በማድረግ ግን የአማራ ህዝብ ታክቲካል ወዳጅ ነዉ። እናም ዮናስ ብሩ በመአዛ መሀመድ ሚዲያ ያደረገዉ ውይይት የአቢይ አህመድ ስትራቴጂያዊ ደጋፊ ሆነዉ ሳለ በሚዲያ ግን ታክቲካል በሆነ መልክ ታክቲካል የተቃዉሞ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በህዝብ አይን ተቃዋሚ መስለዉ ለመታዬት የሚራወጡትን የሚወክል ነዉ። እንዲህ አይነቶቹን ጥንቅቅ አድርገህ የማወቅ ግዲታ የትግሉ አንድ አካል መሆኑን አትርሳ።በሚዲያ ወጥቶ እስክስታ በመምታት ተቃዋሚ የመሰለህን ሁሉ እተቃዋሚ ዝርዝር ዉስጥ ከተህ አብረህ እንዳትሮጥ። ለማንኛዉም ካሁን ብሁላ በኢትዮጵያ የትግል መድረክ ዉስጥ የአጭበርባሪዎች ካባ ቶሎ ቶሎ እሳት እንደጎበኘዉ ጭድ ጭርጭር እያለ የሚቃጠል መሆኑንም አብረህ አንሰላስለዉ። ምክንያቱም ትግሉ ዉስጥ ነገር እግዚአብሄር አለበትና። ሆኖም ካላመንክ ነገረ እግዚአብሄር የሚለዉን ዝለለዉ። የሆኖ ሆኖ ግን ካሁን ብኋላ የተንኮል ካባ የሚለብስ ሁሉ ቶሎ ቶሎ ካባዉ እንደሚገፈፍ ልብ ብለህ ተከታተል።የዮናስ ብሩ ካባ እንዲህ በፍጥነት እንደተገፈፈዉ ሁላ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply