ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ አራት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች “ወርቃምባ” ከተባለች ከተማ እንደሚገኙ ተገለጸ።                  አሻራ ሚዲያ…

ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ አራት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች “ወርቃምባ” ከተባለች ከተማ እንደሚገኙ ተገለጸ። አሻራ ሚዲያ…

ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ አራት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች “ወርቃምባ” ከተባለች ከተማ እንደሚገኙ ተገለጸ። አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-26/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሐዬና ጌታቸው ረዳ በአንድ ቦታ ለይ መሆናቸውን የሰሜን ዕዝ የ31 ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አስታወቁ፡፡ አዛዡ ኮሎኔል ሻምበል በየነ ከፍተኛ አመራሮቹ ያሉበት ቦታ መታወቁን ገልጸው በተምቤን፣ አቢ አዲ እና ወርቃምባ ይገኛሉ ብለዋል በሰጡት መግለጫ፡፡ አመራሮቹ የሚገኙበት ስፍራ ከሃገር መከላከያው በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኝ እና የሰራዊቱ አባላት የቅርብ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙም ነው አዛዡ የተናገሩት፡፡ ኮሎኔል ሻምበል አመራሮቹ በተምቤን አቢ አዲ እንዲሁም የሀውዜንና አድዋ መገንጠያ በሆነችው ወርቃምባ ከተማ ውስጥ መሆናቸውን ማየት ተችሏል ብለዋል፡፡ ወርቃምባ ከሰራዊቱ በ10 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኝ ነች እንደ ኮሎኔሉ ገለጻ፡፡ በልዩ ጥበቃ ማለትም በኮማንዶ ጭምር እተየተጠበቁ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ ከአራቱ ባለስልጣናት ውጭ ሌሎች ብዙም በሕዝብ የማይታወቁ ባለስልጣናት በስፍራው እንዳሉ ስለማየታቸው ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ፈርሷል ያሉት ክፍለ ጦር አዛዡ ሰራዊቱን ከድተው ለህወሃት የወገኑ አባላትን የመያዝ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ጥቂት ቀናትን ብቻ እንደሚወስድ እንደሚወስድም ጠቁመዋል፡፡ ኮሎኔል ሻምበል አያይዘውም ከአራቱ ውጭ ያሉ ሌሎች አመራሮች ደግሞ አዋሳኝ በሆኑ የአማራ ክልል የተከዜ ጫፍ ስፍራዎች በዋናነትም ልዩ ስሙ “አቅመራ” በሚባል ስፍራ ሲመላለሱ መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹ አሁን ላይ ቀለብ፣ ውሃ እና ነዳጅ የላቸውም” ነው ያሉት አዛዡ፡፡ ይህ በመሆኑም እነርሱን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ በአጭር ቀናት ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply