
ለበርካታ አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልል የፖለቲካ መድረክ ላይ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ሥር ሌሎችንም በማካተት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያቋቁም፣ የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቦታቸውን ለማስረከብ እንዳመነቱ ሲነገር ነበረ። በዚህ ጉዳይ፣ በፓርቲያቸው ሕጋዊ ዕውቅና እና በሌሎችም ተያያዥ ርዕሶች ዙሪያ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
Source: Link to the Post