ዶ/ር ደብረጽዮን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አመሰገኑ

https://gdb.voanews.com/022a0000-0aff-0242-0357-08dae772e125_tv_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሃት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራውና ሚኒስትሮችና የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች የተካተቱበት ልዑካን ቡድን በመቀሌ ተገኝተው የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችን በማስቀጠል ላይ ውይይት አድርገዋል።

ልዑካኑ ከትግራይ ክልል መሪ ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤልና በክልሉ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከተወከሉ አካላት ጋራ ተገናኝተው ተወያይተዋል። ዶ/ር ደብረጽዮን የልዑካን ቡድኑን አባላት ያመሰገኑ ሲሆን፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በጣም ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ማመስገን እፈልጋለሁ” ብለዋል።

ዛሬ በመቀሌ የአንድ ቀን ቆይታ ባደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ውስጥ ከተካቱት ባለሥልጣናት መካከል የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የበላይ ኃላፊዎችም ይገኙበታል። ባለሥልጣናቱ የአንድ ቀን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ማምሻውን ተመልሰዋል።

እነዚሁ የኢትዮ-ቴሌኮም፣የመብራት ሃይል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የመንገዶች ባለስልጣን እና የሌሎችም ተቋማት የበላይ ሃላፊዎች አገልግሎት እየተጀመረ ባለበት ሂደትና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

/ዝርዝሩ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply