ጀነረል አርማጌዶን በመባል የሚታቁት ሰርጌ ሱሮቪኪን በዩክሬን ያለውን የሩስያ ጦር እንዲመሩ ተሰየሙ።በደቡባዊ ዩክሬን እና በዶንባስ ያለውን የሞስኮ ሃይል እየመሩ የሚገኙት እኚህ ጀነራል፣ በዩ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/SxCBJ8XdtFBBQ-qiLq6YjJl3qBH_uFpa3ol4l7VauSBCNuQwKW1ED18-lCW67nABgLSw4xeZtK_KUWB4PYEjClpS2Fsd6uOZzSLa2mReRIRW3nTkWdmI2MuughD2sklomtGx4u09QyyJbBkWwyXmjMIkolLzXDjmLu_hiWNDPPgB4GJm7kBPw3TQfOZXSq0UGOppDZ0VY0HiMy_PZgDvtwjQKpQXBUU7KqRW8B8fJVt_jyqV4oerucniQsDTzWj_D7o0B3MLArkoW84DGAN0iYyVQi0TI8vFi9qI4dTo6imti1PtWQn2GjPa3M9IH_HYl9fMTKi06dUi-2ALAHR0Aw.jpg

ጀነረል አርማጌዶን በመባል የሚታቁት ሰርጌ ሱሮቪኪን በዩክሬን ያለውን የሩስያ ጦር እንዲመሩ ተሰየሙ።

በደቡባዊ ዩክሬን እና በዶንባስ ያለውን የሞስኮ ሃይል እየመሩ የሚገኙት እኚህ ጀነራል፣ በዩክሬን ያለውን የሩስያ ሃይል በሙሉ እንዲመሩ ሃላፊነቱ የተጣለባቸው መሆኑን የሩስያ መከላከያ አስታውቋል፡፡

‹‹አርበኛው›› ሲል የገለፃቸው ሚኒስቴሩ ከ2017 ጀምሮ የሃገሪቱን አየር ሃይል ሲመሩ መቆየታቸውን አስታውሷል፡፡

ሞስኮ በደማስቆ ባካሄደችውም ወታደራዊ ተልእኮ ስኬታማነት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል በማለት ሩስያ ጀግና የሚል ማእረግም ያላበሰቻቸው መሆናቸውን ሃላፊነቱ ሲጣልባቸው ተጠቅሷል፡፡

በቅርብ የሚያውቋቸው የጦር መኮነኖች ‹‹ጀነራል አርማጌዶ›› የሚል መጠሪያ የሰጧቸው ጀነራሉ ሱሮቪኪን ውትድርናን ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለመሆናቸው ይመሰከርላቸዋል፡፡

በሌላ በኩል የኔቶ አባል የሆኑ ሃገራት ቃልኪዳኑ ዩክሬንን በቻለው አቅም ሁሉ ሊያስታጥቅ እንደሚገባ እየጠየቁ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ሃገራቱ ያለውን ሁሉ የጦር መሳሪያ እናስታጥቅ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ሩሲያ ከ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት ጋር ጦርነት እየገጠመች መሆኑን ስትገልጽ መቆየቷም ይታወሳል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply