You are currently viewing ጀኔራል አበባው ታደሰ የሸዋሮቢት ሽማግሌዎችን፣ባለሀብቶችን እና ሚሊሻዎችን እያሳፈነ መሆኑ ታወቀ የአማራ ሚዲያ ማእከል ግንቦት 15 2015 አ/ም አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ጀኔራል አበባው…

ጀኔራል አበባው ታደሰ የሸዋሮቢት ሽማግሌዎችን፣ባለሀብቶችን እና ሚሊሻዎችን እያሳፈነ መሆኑ ታወቀ የአማራ ሚዲያ ማእከል ግንቦት 15 2015 አ/ም አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ጀኔራል አበባው…

ጀኔራል አበባው ታደሰ የሸዋሮቢት ሽማግሌዎችን፣ባለሀብቶችን እና ሚሊሻዎችን እያሳፈነ መሆኑ ታወቀ የአማራ ሚዲያ ማእከል ግንቦት 15 2015 አ/ም አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ጀኔራል አበባው ወደ ሸዋሮቢት እና አካባቢዋ በማቅናት ህዝቡን ሰብስቦ “ፋኖ መከታውን አሳልፋችሁ ስጡን፤የምንፈልገው እሱን ነው።የፋኖዎችን መሪ መከታውን ከሰጣችሁን ተጨማሪ ትጥቅ እናስታጥቃችኋለን”በማለት ህዝቡን ሊያታልል ሞክሯል። በጄኔራሉ የጅል ጥያቄ የተገረሙት የአካባቢው ኗዋሪዎች “…ፋኖ መከታው ድምፁ የማይሰማ ጨዋ ልጃችን ነው፤በሸኔ፣በህዎሓት እና በሌሎች ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ስንወረር ቀድሞ የደረሰልን ልጃችን ፋኖ መከታው እና አባላቱ ናቸው።ለመሆኑ ዛሬ እዚህ ምን ልትሰሩ መጣችሁ? ከሸኔ እና ከህዎሓት ጦር የተረፉትን ልጆቻችንን ጦር አዝምታችሁ በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፋችሁ፣ከብቶቻችን ገደላችሁ፣ንብረት አወደማችሁ፣አሁን ደግሞ ዕንቁ ልጃችንን ስጡን ስትሉ አታፍሩም?” የሚል ቆራጥ መልስ ጄኔራሉ ላነሳው የቂል ጥያቄ በመመለስ መሸኘታቸው ይታወሳል። ታዲያ በዚህ የተበሳጨው ጄኔራል አበባው ታደሰና አዛዦቹ ዛሬ ከንጋቱ 11 ጀምሮ የአካባቢው ባላሃብትና ሽማግሌዎችን፣ሚሊሻዎችን እና ነቄ ግለሰቦችን በድንገት ማፈናቸው ተገልጿል። ከታፈኑት መካከል:- 1.አምሜ ጣሰው -የአገር ሽማግሌ ና ባለሃብት 2. ተገኝ አባተ- ሚሊሻ 3. አንበርብር ወንድምሲገኝ እና 4. አቡሽ ሳኒ- የተሰኙ ሚሊሻዎችን አሳፋኗል ሲሉ የታፋኝ ቤተሰቦች ከስፍራው አድርሰውናል። በአፋናው የተበሳጨው የአካባቢው ማህበረሰብ ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply