ጁሊያን ሎፕቲጌ የዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሙ !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ጋር የተለያየው ዌስትሀም ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

ዌስትሀም ዩናይትድ የ 57ዓመቱን የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ፣ ሲቪያ ፣ ዎልቭስ እና ስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌን በሀላፊነት መሾሙን በይፋ አሳውቋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከሀላፊነቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ” እንደ አሰልጣኝ ሁልጊዜ ምኞቴ በየጊዜው መሻሻል ፣ ተጨዋቾችን ማሻሻል እና ትልቅ ነገሮችን ማሳካት ነው ለመጀመር ጓጉተናል ” በማለት ተናግረዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply