ጁንታውን የማደንና በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው መልሶ ማቋቋም ለፈረንሣይ ሴኔት ገለጻ ተደረገ

ጁንታውን የማደንና በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው መልሶ ማቋቋም ለፈረንሣይ ሴኔት ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት ጁንታን የማደንና በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው የመልሶ ማቋቋም ስራለፈረንሣይ ሴኔት ገለጻ ተደረገ።
ለሚደረገው እንቅስቃሴ መንግሥትን መደገፍ እንደሚገባ ለማስረዳት መቻሉን በፈረንሳይ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ገልጿል፡፡
በፈረንሳይ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ እንዳሉት በትግራይ ለተፈጠረው ሁኔታ ብቸኛው ተጠያቂ የጁንታው ቡድን ነው።
የጥፋት ቡድኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አረመኔያዊ ጥቃትና ግድያ መፈፀሙን ማስረዳታቸውን አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲከበር ስኬታማ የሆነ ሕግ የማከበር ተግባር እንደተካሄደና የህወሃት ጁንታ ለፍርድ እንደሚቀርብ አብራርተዋል።
በትግራይ ክልል በመልሶ ማቋቋም ለሚደረገው እንቅስቃሴ መንግሥትን መደገፍ እንደሚገባም መግለጻቸውን አሳውቀዋል፡፡
አምባሳደሩ ለፈረንሣይ ሴኔት እና ለሴኔቱ የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ሴዲሪክ ፔረን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ጁንታውን የማደንና በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው መልሶ ማቋቋም ለፈረንሣይ ሴኔት ገለጻ ተደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply