ጁንታው የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጭምር የበላ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ጁንታው የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጭምር የበላ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ሁለንታናዊ ግንባታ ክልሉ ከፌዴራል መንግስት ጋር ተቀናጅቶ በትብብር እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ጁንታው የተሰጠውን ይቅርታ ወደ ጎን በመተው በንቀት ወደ ክህደት በመግባቱ ራሱን በራሱ በልቷል ብለዋል አቶ ሽመልስ አብዲሳ።

አቶ ሽመልስ እንዳሉት ጁንታው የኦሮሞ ወጣቶች፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች ጭምር የበላ ነው ።

ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ግንባታ የኦሮሚያ ክልል ከፌዴራል እና ከክልል መንግስታት ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

አሁን አልፈን ከመጣነው ችግር በላይ ውስብስብ የሆኑ ማነቆዎች ይጠብቁናል፤ ህዝቡን ከድህነት ማላቀቅ፣ በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ራስን ማብቃት፣ የሀገሪቱን ህዝቦች የምትመስል ሀገርና ሥርዓት መገንባት ላይ አሁንም በትኩረት እንሰራለን ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ሚዲያ የህዝብ ልሳን እንዳይሆን ጁንታው ሲሰራ ነበር ያሉት ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው።

ህግን በማስከበር ሂደት መረጃን ለህዝብ በማድረስ ለተሳተፉ የኦቢኤን ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጥቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ጁንታው የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጭምር የበላ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply