ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት 1 ሚሊየን ብር እና 150 ፍየል ድጋፍ አደረገ

ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት 1 ሚሊየን ብር እና 150 ፍየል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ፍየልና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው 150 ፍየል እና 1 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ሲሳይ አስረክቧል ።

የጂግጂጋ ዩኒቨርስቲ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽንና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ከማል ሀሽም መሃመድና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልህ ሁሴን እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ከደመወዛቸው 10 በመቶ ለመስጠት ወስነዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የደም ልገሳ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት 1 ሚሊየን ብር እና 150 ፍየል ድጋፍ አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply