
የመንግሥትን ጫና በመሸሽ ከተሰደደ በኋላ ከአራት ዓመት በፊት ወደ አገሩ የተመለሰው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዳግም ወደ ስደት ተመልሷል። ለወራት በእስር የቆየው ታምራት በዋስ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ለወራት ድምጹ ሳይሰማ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ከባለቤቱ ጋር ከአገር ወጥቷል። ታምራት አሁን እንዳይጠቀስ ከፈለገው በስደት ካለበት ስፍራ ስለእስሩ፣ በዝምታ ስለቆየበት ምክንያት፣ ስለወደፊት ዕቅዱና ስለሌሎች ጉዳዮች በተለይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል።
Source: Link to the Post