You are currently viewing ጃርዴጋ እና ሰቀላ ላይ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በሰላማዊ አማራዎች ላይ ጦርነት ከፍተው እየገደሉ እና እያፈናቀሉ ያሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው የጃርዴ…

ጃርዴጋ እና ሰቀላ ላይ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በሰላማዊ አማራዎች ላይ ጦርነት ከፍተው እየገደሉ እና እያፈናቀሉ ያሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው የጃርዴ…

ጃርዴጋ እና ሰቀላ ላይ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በሰላማዊ አማራዎች ላይ ጦርነት ከፍተው እየገደሉ እና እያፈናቀሉ ያሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው የጃርዴጋ ከተማን ተቆጣጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጃርዴጋ እና ሰቀላ ላይ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በሰላማዊ አማራዎች ላይ ጦርነት ከፍተው እየገደሉ እና እያፈናቀሉ ያሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው የጃርዴጋ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከከተማው ለመውጣት ያልቻሉ አማራዎችን እያሳደዱ በመግደል እና በማፈናቀል፣ በመዝረፍ እና በማቃጠል ላይ ስለመሆናቸው በየጫካው እየተሯሯጡ ያሉ አማራዎች ተናግረዋል። ታህሳስ 1/2015 ከሻምቡ የመጣውን ከ20 መኪና በላይ ዘመናዊ እና የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ጥምር ጦር ከንጋት ጀምሮ ሙሉ ቀን የሰቀላ እና የጃርዴጋ ዙሪያን አማራ ሲገድልና ሲያፈናቅል ከዋለ በኋላ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የጃርዴጋ ከተማን ተቆጣጥሯል። ወደ ገጠር ቀበሌዎች አቅንቶ አማራዎችን ለማጥቃትም ተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥምር ኃይል ከነቀምት በኩል ወደ ጃርዴጋ እየተጓጓዘ መሆኑን የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። ጃርዴጋ መስከረም 12/2015፣መስከረም 14/2015 እና ህዳር 13/2015 ከባድ የወረራ ጦርነት ከፍተው ለመቆጣጠር ባለመቻላቸው ከፍተኛ ቁጣ ስለነበራቸው ንጹሃንን በጭካኔ እያጠቃ መሆኑ ተገልጧል። የጃርዴጋ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ሰሚ አላገኙም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply