ጃፓን የዓለማችን ትልቁ የኒውክሌር ጣቢያን ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች።

የጃፓን የኒውክሌር ኃይል መቆጣጠሪያ ከሁለት ዓመት በፊት በቶኪዮ ኤሌክትሪክ ኃይል ካሺዋዛኪ-ካሪዋ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ላይ ጥሎት የቆየውን እገዳ በማንሳት እንደገና እንዲጀመር ፍቃድ ሰመስጠቱን አስታውቋል ።

ጣቢያው 8 ሺህ 2 መቶ 12 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ተቋም ነው።
አሁን ላይ ይህ ማመንጫ ወደ ስራ እንዲገባ ከሀገሪቱ መንግስት ፍቃድ እንዳገኘ ሮይተርስ ዘግቧል።

2011 በፉኩሺማ በደረሰው የሱናሚ አደጋ ምክንያት በርካታ የኒኩሌር ጣቢያዎችን ዘግታ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በልዑል ወልዴ

ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply