ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ

ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ በሀራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክእስር ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መስማማታቸውን ገለፁ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በህገ ወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጠው የገቡ ኢትዮጵያወያን እስረኞች እንደሚገኙ በመግለፅ እስረኞችን ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።

በነፃ ከእስር ይፈታሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሀገራቸው ግንባታ ይሳተፋሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያውያኑን ዛሬ ከፈለጉ ወደ ሀገራቸው መሄድ ይችላሉ ሲሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ከእስር ለሚለቀቁት የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንደሌለ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወቅር ዘውዴ በበኩላቸው ከፕሬዚዳንት  ጆሴፍ ማጉፊሊ ጋር  በኢንቨስትመንት አመራጮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

እንዲሁም የስዋሊ ቋንቋ በኢትዮጵያ ለማስተማር ዝግጅት መደረጉ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በአፍሪካ ወሳኝ የሆነው ስዋሊ ቋንቋ መምህራንን ለመቀበል ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ምርት ስኬታማነት ልምድ እንደምትወስድም ተናግረዋል።

 

በኤፍሬም ምትኩ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply