በአመራር ላይ የበዛ ልምድ የላቸውም የተባሉት የሉዊዝያና እንደራሴ ጆንሰን ውዝግብ ከበዛባቸው የምርጫ ዙሮች በኋላ ነው ዛሬ 220 ለ209 በሆነ ድምፅ የተመረጡት።
የቀደሙት አፈጉባዔ ኬቭን ማካርቲ ከሥራቸው ከተነሱ ከመስከረም 22/2016 ዓ.ም. አንስቶ ላለፉት ሃያ ሁለት ቀናት በሪፐብሊካኑ አብላጫ መቀመጫ የተያዘው የተወካዮች ምክር ቤት ያለመሪና ያለሥራ ተሽመድምዶ ቆይቷል።
ምክር ቤቱ እሥራዔል ሃማስ ላይ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለሚያካሂዷቸው ጦርነቶች መደገፊያ እንዲውል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጠየቁትን የ106 ቢሊዮን ዶላር በጀት ተመልክቶ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
Source: Link to the Post