ቁምቡላን በቁምቡላ ይመለሳል! በአንድ አገር ምርጫ በመደረጉ ዴሞክራሲ አይገነባም አዲሶቹ አንባገነኖች በዴሞክራሲ ስም ህዝብ መረጠን ለማለት ምርጫ በማድረግ የዓለምን ህብረተሰብና መንግሥቶችን አንባገነን መሪዎች ያጭበረብራሉ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ለአለፍት 27 ዓመታት በአምስት ዙር ምርጫ ወያኔ በምርጫና በዴሞክራሲ ስም በአንባገነንነት ነግሶል፡፡ በዓለማችን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥት ይሄዳል፣ መንግሥት ይመጣል፣ በሃገራችን የይስሙላ ምርጫ ህወሓት ኢህአዴግ የአንድ አውራ ፓርቲ መንግሥት አምስት ዙር ምርጫ አሸናፊ በመሆን ያለተቀናቃኝ ገዝቶል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢና አባላትም ከገዢው ወያኔ መንግስት ጋር በማበር ከፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ሳይሆኑ ህዝብና ሀገር ሸጠው አንባሳደር ሆነው ተሸመው አተላ ታሪካቸውን አፅፈዋል፡፡ የ1997 ዓ/ም ምርጫ ሁለት መቶ ዜጎች ተገድለው፣ አምስት ሽህ ሰዎች ቆስለው፣ ሰማንያ ሽህ ዜጎች በእስር ቤት ታጉረው ለደረሰ ጉዳት ዛሬም ንስሃ አልተገባም አጣሪ ኮሚቴው ዳኛ ፍሬህይወትና ዳኛ ወልደሚካኤል ያጣሩትን የምርጫ ውጤት ለፓርላማና ለህዝብ እንዳያቀርቡ ተደርገዋል፡፡ ለ1997ዓ/ም የምርጫ ወንጀል ተጠያቂዎች የፖሊስ ኮሚሽነሩ ወርቅነህ ገበየሁና ሌሎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ምርጫ በምርጫ፣ ቁምቡላን በቁምቡላ ይመለሳል! የምንለው፣ ላለፉት 27 ዓመታት ወያኔ/ኢህአዴግ በምርጫና በዴሞክራሲ ስም ነግሶ ነበር፡፡ ይህንንም ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የተሳተፉበትን የህዝብ ልጆች ያለቁበትን ይዘነጋሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ነገም በሚደረግ የዘር ምርጫ፣ ከክልሌ ውጡ፣መጤዎች ይውጡ በማለት ምርጫውን ለማሸነፍ የሚደረጉ ትያትሮች ብዙ ንፁሃን ዜጎች ላለማለቃቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያጠናው ካለ ለህዝብ ቢያቀርብ ዋስትናችን ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን ሰብሳቢ በመሆን ያገለገሉ በቦርዱ ድረ-ገፆች እንኮን ከ አንደኛ እስከ ስድስተኛ ምርጫ አጭር ታሪክ አለመገለፁ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ አድርባይ ሹማምንቶች ሆን ብለው የሠሩት ሸፍጥ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ አሰፋ (1ኛ ዙር)፣ ተስፋዬ (2ኛ ዙር)፣ ታዬ አፅቀስላሴ (3ኛ ዙር)፣ ፕሮፊሰር መርጊያ በቃና ጎንፋ ከ2010 (4ኛ ዙር ) እስከ 2015 (5ኛ ዙር) ዛሬ ደግሞ ብርቱካን ሚደቅሳ (6ኛ ዙር) ሲሆኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን ታሪክ በድረ ገፃችሁ ላይ የስድስቱን ዙር የቦርዱን ሰብሳቢዎችና አባላቶችን ለህዝብ ማስተዋወቅ የኮሚሽኑ ሥራ ይመስለናል፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በየክልሎቹ የሚካሄዱ የዘር ፊዴራሊዝም ምርጫዎች ጊዜት የሥነ-ህዝብ ለውጥ (የዲሞግራፊ ) የአንዱን በመጨመርና የአንዱን በመቀነስ ላይ የተመሠረተ የዘር ማፅዳት (ጆኖሳይድ) በማድረግ በምርጫው ለማሸነፍ የሚደረግ የክልል ጦር አበጋዞች ስራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት አለ ብሎ ምርጫ እንዲደረግ ሲተጋ ማየት ምርጫ ተደረገ አልተደረገ የዓለም አቀፍ ህብረተሰብና መንግስቶችን ድጋፍና እርዳታ ለመቀራመት ካለ ፍላጎት አንፃር ካልሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደ ኢዜማና ብልፅግና ፓርቲ ለማዋለድ ታስቦ እንዳልሆነ መገንዘብ ይበጃል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግናና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫው ወቅት የህዝብን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥና በምርጫው በሠላማዊ ሁኔታ መጠናቀቅ ተጠያቂነታቸውን ለህዝብ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ምርጫ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳልመጣና ህወሓት ኢህአዴግ አንባገነናዊ ፈላጭ ቆራጭ የጦር አበጋዞች መንግስት በምርጫ ስም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንባገነናዊ አስተዳደር እንዲመሠረት በማድረግ ተሳታፊ የሆኑ አድርባይ ምሁራን ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ ህወሓት፣ ኦነግ ሸኔና፣ ጉሙዝ ፓርቲን በሽብርተኛነትና በጆኖሳይድ ወንጀለኝነት መፈረጅ አለባቸው እንላለን፡፡
- በቤኒ-ሻንጉል ክልል የኦሮሙማና የጉሙዝ የጦር አበጋዞች የአማራ ዘር የማጥፋት ዘመቻ ቀጥሎል፡፡
- በኦሮሚያ ክልል የጦር አበጋዞች በወለጋ፣ በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ የአማራን ዘር የማጥፋት፣ በድሬዳዋና በአዲስአበባ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የኦሮሙማን ለማስፋፋት የኦዲፓ ብልፅግና የሥነ ህዝብ የማስፈር ዘመቻ በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ ታዬ ደንዳ፣ ከኦነግ ጦር አበጋዞች ጋር በከተሞቹ በምርጫ ካላሸነፉ የዘር ፍጅት ለመፈፀም አይመለሱም፡፡ ደብረዘይት፣ ናዝሬት፣ አሰላ፣ ጅማ ወዘተ ከተሞች ለጥቃት የተጋለጡ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የክልልነትና የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልል የተፈለፈሉና የሚፈለፈሉ አዲስ የጦር አበጋዞች መንግሥት ለአንዱ ስጥቶ ላንዱ ነፍጎ የሲዳማ ክልላዊ መንግስትነት አፅድቆ፣ የወላይታ የማንነት ጥያቄ አሳድሮታል፡፡ የተሠው የሲዳማና ወላይታ ተወላጆች ፍጅት የትላንት ትውስታ ሲሆን ነገ ደግሞ በሌሎቹ አስራ ሁለት የሚደርሱ የክልል አስተዳደርና የማንነት ጠያቂዎች ‹‹ወጣ ወጣ ያለች ማሽላ፣ አንድም ለወፍ፣ አንድም ለወንጭፍ!!!›› እየተባሉ መቀጠፋቸው አይቀሬ ነው፡፡ በደቡብ ክልል ጣረሞት አንጃቦ እናስተውላለን ምሁራን ይሄን እልቂት ለማስቀረት በርትተው ካልሰሩ በኦሮሙማ የዛር በሽታ እንደ ህዳር ሲታጠን ከዘር ፖለቲካ ወጥተን የሚያባላንን የወያኔ ህገ-መንግሥት መቀየር፣ የክልሎች ድንበር ና ወሰንን በማጥፋት፣ ህዝቡ በፈለገበት ቦታ የመኖር ነፃነቱ፣ ተዘዋውሮ የመሥራት ነጻነቱ ሊረጋገጥለት ይገባል እንላለን፡፡ ሽፈራው ሽጉጤ በአማራ ህዝብ ላይ የጉራፈርዳ የዘር ማፅዳት የፈፀመው የሥነ-ህዝቡን ቁጥር ብልጫ በምርጫ በማግኘት ነበር፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (መኢብን) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)ን ጨምሮ 26 ተፎካካሪ ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታወቀ፡፡ ቦርዱ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን የሰረዘው፣ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 ድንጋጌ መሠረት፣ ፓርቲዎቹ ማሟላት የሚገባቸውን ግዴታዎች ባለማሟላታቸው መሆኑን፣ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ:-ከመንግሥት ፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ነው ወይ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ:-የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ መቼ ተደረገ? ማንን በሊቀመንበርነት፣ በምክትል ሊቀመንበርነት፣ በኦዲት ኮሚሽንነት መረጡ፣ የምክር ቤቱ አባላት እነማን ናቸው፣ የመሳሰሉትን ጥየቄ በግልፅነትና በተጠያቂነት ለህዝብና ለሌሎች ተወዳዳሪ ፓርቲዎች መግለጽና ማሳወቅ ባለመቻላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከመንግሥት ፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ አይደለም እንላለን፡፡ በምርጫ ቦርድ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የብልፅግና ፓርቲ እውቅና በቦርድ አግኝቶል ወይ?
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ጉዳይ፣ ህወሓት በሽብርተኛነትና በዘር ፍጅት ድርጊት የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅውቅና ሳይነሳና የፖለቲካ ፓርቲነት ሳይሠርዝ ሃያ ሰባቱ ፓርቲዎች ሲሠርዙ የቦርዱ በደመነፍስ የሚንቀሳቀስ (ዞንቢነት) ያሳያል እንላለን፡፡ መንግሥት ህወሓት/ወያኔን ካልፈረጀው ቦርዱ በምን እዳዬ እፈርጃለሁ ያለ ይመስላል፡፡‹‹ተው ልመድ ገላዬ፣ ትቶህ ለሄደ ሰው አትበል ከለላዬ›› ዘፈን ቢመረጥለት ይነቃ ይሆን ቦርዱ በእራሱ እግር ይቁም!!!
- የመገናኛ ብዙሓን አጠቃቀም በተመለከተ ብልፅግና ፓርቲ በመንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅር መጠቀም፣ በመገናኛ ብሁሃን ሬዲዬና ቴሌቪዥን ስርጭት በይፋ ቅስቀሳ ሲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቃውሞ ድምፁን ሲያሰማ አልተሰማም፡፡ ኢዜማ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝንና(ኢሳት) በማህበራዊ ሚዲያ ‹አባይ ሚዲያ› በመሳሰሉት የቅስቀሳ ስራ መስራቱ፣ ኦፌኮ በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) የቅስቀሳ ስራ መስራቱ፣ ወዘተ በፓርቲዎች ውድድር የመገናኛ ብዙሓን አጠቃቀም ፍህታዊነትና ዕኩልነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወረቀት ላይ ካልሆነ ይዞ መገኘት ያለ ነው የሚመስለው፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ:-የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፡-የህሊና እስረኞች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ይፈቱ!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
‹‹ደግሞ ማወቅ ማለት…..
ከውጭ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ
ከውስጥ የበራውን፤ እንዲወጣ ማድረግ….›› ገብረክርስቶስ ደስታ