ጆ ባይደን – ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት

ጆ ባይደን 46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት በፔንሳልቫንያ ግዛት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጫውን ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን 270 የምርጫ ወረዳ ድምፅ ማሳካት ችለዋል። ይሁን እንጂ በአላስካ፣ ኔቫዳ እና ኖርዝ ካሮላይና የድምፅ ቆጠራው እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል።ባይደን በ4 ሺህ ድምፆች ብቻ እየመሩ በሚገኙበት ጂኦርጂያ ግዛት፤ የድጋሜ ድምፅ ቆጠራ ሊደረግ እንደሚችል ይጠበቃል።አወዛጋቢው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጂኦርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ እና ዊስኮንሰን ግዛቶች የድምፅ መጭበርበር ተካሂዷል በማለት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ መክፈታቸውን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።ዩናይትድ ስቴትስን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት መመለስ እና አገሪቱ ከዚህ ቀደም የነበሯትን የፀጥታና ፀረ ሽብር ስምምነቶች ማስቀጠል ባይደን ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጧቸው ጉዳዮች እንደሚሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያ የዋሺንግተን ዋነኛ የአፍሪካ አጋር የነበረች ሲሆን ግንኙነቱ በባይደን ዘመን የበለጠ እንደሚጠናከር ይጠበቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply