ጆ ባይደን በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሀገራት ስብሰባ ላይ ሊሳተፉ ነው፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሀገራት ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ሮይተርስ ዜና ወኪል እ…

ጆ ባይደን በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሀገራት ስብሰባ ላይ ሊሳተፉ ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሀገራት ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡

ሮይተርስ ዜና ወኪል እንዳስነበበው በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሀገራት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ አትቷል፡፡

በፕሬዝዳንቱ የተመራ ሉኡክ እና ባለስልጣኖቻቸው በነገው እለት ስብሰባው ወደ ሚከናወንበት ስፍራ ያቀናሉም ሲል ነው ሮይተርስ ያስነበበው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከስብሰባው በተጨማሪም ከተለያዩ የምስራቁ ሀገራት መሪዎች ጋር የተናጥል ውይይት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በተለይም በሰሜን ኮርያ የባልስቲክ ምሳኤል ጉዳይ እንደዚሁም በቻይናና በሀገራቸው ያለውን የንግድ ሽኩቻ በሚፈቱበት መንገድ ዙርያ ሰፊ የሆነ ምክክር ሊያደርጉ የሚችሉበት አጋጣሚ መኖሩን የዜና ወኪሉ ያስነበበው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply