‘ገሪላ’ እንዳይጠፋ በሩዋንዳና ኮንጎ ማኅበረሰቦች እንክብካቤ እየተደረገለት ነው

https://gdb.voanews.com/03370000-0aff-0242-d5f1-08daecea333d_tv_w800_h450.jpg

በአካባቢያቸው ውጥረት ቢንገስም በሩዋንዳና ኮንጎ ያሉ ማኅበረሠቦች በሁለቱ ሀገሮች ድንበር አካባቢ የሚገኘውን የዝንጀሮ ዝርያ ያለውና፣ ከገመሬ ዝንጀሮም ተለቅ የሚለውን፣ ፈርንጆቹ ‘ገሪላ’ የሚጠሩት የዱር እንሥሣ እንዳይጠፋ በመንከባከብ ላይ ናቸው።

በኮንጎ ዴሞክራቲል ሪፐብሊክ እና በሩዋንዳ መካከል ባለው ውጥረት ምክንያት በሁለቱ ሀገሮች የሚገኘው ‘ገሪላ’ የዝንጀሮ ዝርያ አደጋ ላይ ወድቋል። ውጥረቱ ቢኖርም ታዲያ በድንበር አካባቢ ያሉ የሁለቱም ሀገሮች ማኅበረሰቦች ገሪላዎቹን ጠብቆ ለማቆየት ተባብረው እየሠሩ ነው።

የቪኦኤው ሰናኑ ቶርድ ከሩዋንዳ የላከውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply