ከየካቲት እስከ የካቲት ሀገራዊ የታክስና ጉምሩክ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ ከየካቲት 23 ጀምሮ ሊያስጀምሩ ማሰባቸዉን በዛሬው እለት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳዉቀዋል።
ንቅናቄው የገቢ ዕድገቱን ለማስቀጠል እና የግብር ከፋዮችን የህግ ተገዥነት ደረጃ ለማሻሻል ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
“ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ከተያዘዉ የየካቲት ወር ጀምሮ እስከሚቀጥለዉ ዓመት የየካቲት ወር ድረስ እንደሚቆይ ነው የተገለጸው።
የጉምሩክ ኮሚሽን በርካታ ሪፎርሞች ማድረጉን የገለፁት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣
የንግድ ማህበረሰቡን፣ህዝቡን፣ምሁራኑን፣የሃይማኖት ተቋማትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የድርሻቸዉን ሚና እንዲወጡ የታሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ንቅናቄው በማህበረሰቡ፣ከክልል እና ፌደራል ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት፣የመንግስት ተቋማት፣ የሙያና የንግድ ማህበራት እንዲሁም ከሚዲያዎች ጋር ጭምር መድረኮች እንደሚፈጠሩ በመግለጫዉ ተነስቷል።
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እንደገለጹት፣ ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተቻለ መጠን ለማስተካከል እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሚኒስቴሯ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ አሰራሩን በማዘመን ወደ ዲጂታል የሚደረገዉ ሽግግርን እያፈጠነዉ ነዉ ብለዋል።
ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽኝ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ከንቅናቄው ማህበረሰቡ የቀረጥ እና ታክስ ጠቀሜታን ተረድቶ ለሀገር ዕድገት አስተዋፅኦ የሚያደርግበትን ወጤት እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።
በአቤል ደጀኔ
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post