“ገናን በላሊበላ” – የአማራ ክልል መርኃግብር

በጦርነቱ ምክንያት የተዳከመውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ማነቃቂያ ሥራዎች መጀመሩን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው “ገናን በላሊበላ” በሚል መሪ ቃል የገናን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ ላሊበላ ከተማ ላይ ለማክበር ዝግጅት መጀመሩን ገልጿል።

የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ “የህወሓት ታጣቂዎች በአካባቢው በሚገኙ የመሠረተ ልማት አውታሮችን አውድመዋል” ብለዋል።

መንግሥት፣ ባለሃብቱ፣ የሚመለከታቸው አካላትና ማኅበረሰቡ የጎደለውን በማሟላት በዓሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ እገዛ እንዲያደርጉ ኃላፊው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply