
ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን የመቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ትግራይ ላለፉት 11 ወራት ያህል የባንክ፣ የስልክና ሌሎች መሠረታዊ አግልግሎቶች እንደተቋረጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት ብችግር ውስጥ ላሉ ለቤተሰቦቻቸው ገንበዘብ መላክ የሚፈልጉ ሰዎች፣ ከሚልኩት ብር ወደ ግማሽ የሚጠጋውን ገንዘቡን ለሚያደርሱ ሰዎች ለመክፈል ተገደዋል።
Source: Link to the Post