You are currently viewing ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና ሌሎች አንዳንድ ተቋማትም  ሰራተኞች ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከለከሉ።…

ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና ሌሎች አንዳንድ ተቋማትም ሰራተኞች ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከለከሉ።…

ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና ሌሎች አንዳንድ ተቋማትም ሰራተኞች ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከለከሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና ሌሎች አንዳንድ ተቋማትም ሰራተኞች ጥቁር ልብስ ለብሰው እንዳይገቡ ሰራተኞችን ከልክለዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ መላው የተዋህዶ ልጆች ጥቁር ልብስ በመልበስ ጾመ ነነዌን በጾም በጸሎት እንዲያሳልፉ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ እነዚህ እና መሰል ተቋማት ጥቁር ለብሳችሁ አገልግሎት እንዳትሰጡ ሲሉ ሰራተኞችን ከልክለዋል። የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሠራተኞች በሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሶ መስራትን ከልክሏል። “በወቅታዊ ጉዳይ ተያይዞ መንግስት መስሪያ ቤት ጥቁር ልብስ ለብሶ ሥራ መስራት የተከለከለ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡” ሲል ገልጧል። ስለሁኔታው ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት ይህን አጋርቷል:_ ጥቁር ልብስ ለብሰው አገልግሎት ለማግኘት ወደ መንግስት ተቋማት የሄዱ ዜጎች እንዲመለሱ እየተደረገ እንደሆነ ዛሬ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። “ከበላይ በመጣ ትእዛዝ” በማለት እንደ ገቢዎች፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ ፍርድ ቤት… ወዘተ ያሉ ተቋማት በዚህ መልኩ ሰዎችን እየመለሱ እንደሆነ ታውቋል። በተጨማሪም፣ በዛሬው ሱባዔ ላይ ካራቆሬ ባለው የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ በመልበስ የሄዱ በሙሉ ለእስር እንደተዳረጉ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply