You are currently viewing ገንዘብ ሚንስቴር ከውጭ የሚገቡ 38 ዓይነት ምርቶች ለጊዜው የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቀድላቸው መወሰኑን አስታውቋል። መንግሥት በጥናት ላይ ተመስርቶ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ የውጭ ምንዛሬን የቅድሚያ…

ገንዘብ ሚንስቴር ከውጭ የሚገቡ 38 ዓይነት ምርቶች ለጊዜው የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቀድላቸው መወሰኑን አስታውቋል። መንግሥት በጥናት ላይ ተመስርቶ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ የውጭ ምንዛሬን የቅድሚያ…

ገንዘብ ሚንስቴር ከውጭ የሚገቡ 38 ዓይነት ምርቶች ለጊዜው የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቀድላቸው መወሰኑን አስታውቋል። መንግሥት በጥናት ላይ ተመስርቶ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ የውጭ ምንዛሬን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የምግብ ሸቀጦች፣ መድሃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶች ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነ ለብሄራዊ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል። የውጭ ምንዛሬ እንዳይሰጣቸው እገዳ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል፣ ውስኪና ሌሎች የአልኮል መጠጦች፣ ከሕጻናት አልሚ ምግብ ውጭ ያሉ የታሸጉ ምግቦች፣ ሽቶ፣ መስቲካ፣ ቸኮሌት፣ ውሃ፣ ሲጋራ፣ ምንጣፍ፣ ሰው ሰራሽ ጸጉር እና የቤት አውቶሞቢሎች ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply