ገዢው ፓርቲ ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽ ለዘመናት የፈጸመችውን ሴራ በመቃወም ኢትዮጵያውያን ለሀገራዊ አንድነት እንዲቆሙ እያሳሰቡ ናቸው፡፡

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ግብጽ ሴራዋን ቀድሞ በነበሩት የተለያዩ መንግስታቷ ስትፈጽመው የቆየች እንደሆነ እና ኢትዮጵያ በፍትሐዊነት ሃሳብ ላይ የምታተኩር የዓባይ ወንዝንም በእኩል ተጠቃሚነት እንደምታምን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስነብቧል፡፡

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡ የኅብር ኢትዮጵያ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና የፖለቲካ ሃይሎች ያለ ልዩነት በአንድ ያስተሳሰረ እንደሆነ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ፓርቲ /ኢዜማ/ የኮምዩኒኬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ በበኩላቸው ግድቡ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃብት እንደተሰራ እና የውጭ ሃይሎች ጫናን ለማስቆም በኢትዮጵያዊ መንፈስ የአንድነት ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው የግብጽ የግብርና መሰረት የዓባይ ግድብ በመሆኑ ግብጽ የውሃ ክፍፍሉ ፍትሐዊ አይደለም በማለት ለዘመናት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ባለመፈለግ ሴራ ውስጥ እንደተጠመደች አስገንዝበዋል፡፡

ፓርቲዎቹ የፖለቲካ ርዕዩት አለም ልዩነትን ከህዳሴው ግድብ አርቀን ለአገራዊ አንድነት እና የዜጎች ጥቅም መከበር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ቀን 23/09/2019

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post ገዢው ፓርቲ ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽ ለዘመናት የፈጸመችውን ሴራ በመቃወም ኢትዮጵያውያን ለሀገራዊ አንድነት እንዲቆሙ እያሳሰቡ ናቸው፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply