ገዳም ውስጥ የነበሩ “አራት አባቶች በታጣቂዎች” ተገደሉ!

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ እራሱን “ኦነግ ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታወቀች።

የቤተ ክርስቲያኗ የህዝብ ግንጙነት መምሪያ መረጃ እንደሚያመለክተው የካቲት 11 ቀን 2016 ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ተጨማሪ አባቶችን እና የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሙ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያዎች በቡድኑ በመወረሳቸው ምክንያት ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገዳማውያኑ በስጋት ላይ መሆናቸውም የተገለጸ ሲሆን፤ የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)
፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)
፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)
፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply