ገዳ ባንክ ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው እለት ፈፅሟል።ባንኩ የባንክ አገልግሎት አሰራሩን ከወንጀል ንክኪ የፀዳ ለመ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/jAJ2Em_c5FO4M4UJe_fUnWBngqcP5GjrmlD73OU9bjUYSedkbbbu0mRIJ5IQMyGJ19gCQE6x0wS0kytzY66PQfWkOYSlgeZUKKN0J8PdLOIhO87vPpZdRvj9CnMSysn3VjY2uu8Fz9IJMbJHsOGhbj7rqZ3Qd6Igk6-LODpWwDTyoxoEsAZDtncqj0KZQFEBT282c5Y1f260GaPOsDgR83ocL6Zbmbk6B3uAIgZRB8goF-kQcTdgxZ0d_jv9LbvkEOzmuy9dbcHqyP3Jl-CEfKhlL0bgVF7N6OUXVilb58UVfuc15VOmydh8_sdCOFn_pERwM8gqs364HqLA-avt0A.jpg

ገዳ ባንክ ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው እለት ፈፅሟል።

ባንኩ የባንክ አገልግሎት አሰራሩን ከወንጀል ንክኪ የፀዳ ለመድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጋር ተፈራርሟል ።

ስምምነቱ ከሰነዶች ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ እና ህጋዊ ተግባራትን ለማበረታታት ይረዳል ሲሉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቱ ተናግረዋል ።

አክለውም አገልግሎቱ አሁን ላይ በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ብልሹ አሰራሮችን ከማስቀረት ባለፈ ጊዜን እና ገንዘብን መቆጠብ መቻሉን አንስተዋል ።

ገዳ ባንክ ከተቋሙ ጋር ያደረገው ስምምነት የዚሁ ሂደት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

በስምምነቱ ላይ የተገኙት የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ደገቶ ኩምቤ፣ ከሰነዶች ህጋዊነት ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት በርካታ ወንጀሎች ይሰሩ እንደነበር ገልጸዋል ።

አሁን ላይ ግን አገልግሎቱን ማዘመን በመቻሉ በርካታ ችግሮችን መቅረፍ ተችሏል ነው ያሉት።

አገልግሎቱ አሁንም ወንጀሎችን መከላከል እንዲያስችለው መግሥትን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ዳይርክተሩ አስታውቀዋል ።

በመሳይ ገ/መድህን

ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply