ገዳ ባንክ የ ኤት ኤም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበረ የሚገኘው ገዳ ባን የኤት ኤም ማሽን አገልግሎት ማስጠቀም መጀመሩን የባንኩ ፕሬዚዳን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Dn0wciAbzr60MCmzfuYH65VQZX708k8LqM3MrvFtdhB2ev34oT3Fsnk_4FekSRdHXTwNITMlKuOih35eITeS74Nxr4cznyrrOpUpqMQZgoCAMNkIzfSfX_D2eznnwfjhi91EoIQYGO_XcRg2hKMb9lc3uvu3z0BrtWULklTi_43wRCqb3_83Sjmql0Dfthhzm_K4dDQEV9dbMHLfWhndonXr9eUiuCmEMp4m2-xKLVbfr7I6jCo0m9rd2YYGT6qr5qL_twyinwe-SdQROeCWUzkQvYLIGt_ZB0eRPB801E4_ykXTUoC5zOaugfgz8CvgRbVX07YTUpvpa0QuaMIiUA.jpg

ገዳ ባንክ የ ኤት ኤም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበረ የሚገኘው ገዳ ባን የኤት ኤም ማሽን አገልግሎት ማስጠቀም መጀመሩን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወልዴ ቡልቶ ተናግረዋል ።

ደንበኞች የኤት ኤም አገልግሎት የሚያገኙበት ጂ-ካርድ የተሰኘ ካርድ መዘጋጀቱን አንስተዋል ።

ባንኩ የኤት ኤም አገልግሎቱን ከኢትስዊች የባንክ ሲስተም ጋር ያገናኘ ሲሆን የገዳ ባንክ ደንበኞች ከዛሬ ጀምሮ በማንኛውም ባንክ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል ።
ገዳ ባንክ በተመሰረተ በአንድ አመት ውስጥ ተቀማጭ ገንዘቡን ከ 3 ቢሊየን ብር በላይ ማሳደግ መቻሉን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

ባንኩ አሁን ላይ ቅርንጫፎቹን ወደ 73 ያሳደገ ሲሆን ከ1ሺህ 1 መቶ በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አንስተዋል ።

ነገር ግን አሁን ሃገሪቱ ላይ ካለው የሰላም ችግር የተነሳ ቅርንጫፍ ለመክፈት አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች መኖራቸውን አቶ ወልዴ ቡልቶ ተናግረዋል ።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩ የገለፁት አቶ ወልዱ አነዚህም መካከል ሴቶችን የሚያበረታታው “ስንቄ የቁጠባ አገልግሎት ” እና የልጆችን የቁጠባ በህል ለማሳደግ ይረዳሉ የተባሉት “ደበሌ እና ጋሜ” የተሰኙ የባንክ አገልገሎቶች ይገኛሉ ብለዋል።

ገዳ ባንክ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበረ ሲሆን የደንበኞቹን ቀጥር ወደ 1 መቶ 70 ሺህ ማሳደግ መቻሉን አስታውቋል ።

በመሳይ ገብረ መድህን

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply