You are currently viewing “ጉራጌ ክልል እንዲሆን ትደግፋላችሁ” በሚል የታሰሩት የምክር ቤት አባላት፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

“ጉራጌ ክልል እንዲሆን ትደግፋላችሁ” በሚል የታሰሩት የምክር ቤት አባላት፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

“ጉራጌ ክልል እንዲሆን ትደግፋላችሁ” በሚል የታሰሩት የምክር ቤት አባላት፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ “ጉራጌ ክልል እንዲሆን ትደግፋላችሁ” በሚል የታሰሩት የምክር ቤት አባላት፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ፍርድ ቤት መጋቢት 5/2015 ቀርበዋል። በተጨማሪም በፌዴራል ፍርድ ቤት ጊዜ ቀጥሮ ለምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ፖሊስ ህገ ወጥ በሆነ ሁኔታ ለጉራጌ ዞን ፖሊስ ያስረከባቸው እነ ጀንበር አብዶ (6 ሰዎች)በሚል መዝገብ ተከፍቶባቸው የነበሩት የህሊና እስረኞች እንዲሁ ቡታጅራ ከተማ ፍርድ ቤት ፖሊስ አቅርቧቸዋል። በተያያዘ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል የብሄረሰብ ምክር ቤት አባል ስለሆኑ በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ ፖሊስ እንዲለቃቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ ከእስር ተፈትተው የነበሩት እና በኋላም ደህንነቶች አስረው ለጉራጌ ዞን ያስረከቡት አቶ መኑር ረሺድ እንዲሁ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤቱም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባል የሆኑት ወ/ሮ ጠጄ ታደሰ እና የደቡብ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ መኑር ረሺድ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ሌሎች የህሊና እስረኞችን በተመለከት ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። መረጃው ጠበቃ ቶፊቅ በድሩ መሆኑን በመግለጽ የዘገበው Emat Gurage Media ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply