በኢትዮጵያ የህፃናት እጣ ፈንታ እንዲህ ነው!!! በባህር ማዶ አገራት ‹‹ምርጥ ምርጡን ለህፃናት!››ነው፡፡
የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የኦሮሞ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት በማገት ህጣናት ልጆቹን ከቤተሰባቸው ነጥቆ ባልበላ አንጀታቸው መሣሪያ አስታጥቀዋቸው በርሃ ያንከራትቶቸዋል፣ ከትምህርት ገበታቸው አሰተጎጉለው ገዳዬችና አራጆች እንዲሆኑ ፈርደውባቸዋል፡፡ የኦነግ መሪዎች ልጆቻቸውን አውሮፓና አሜሪካ እያስተማሩ የደሃውን ልጆች በጥላቻ አጥምቀውት ወርቃማ እድሜውን ሠርቀውታል፡፡ ኦነግ ሰዎች ያርዳል፣ ሴቶች ይደፍራል፣ ባንክ ይዘርፋል፣ ሴት ተማሪዎች አግቷል፣ይሄን ወንጀለኛ ድርጅት በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court) ቀርቦ ፍርድ እንዲያገኝ ማድረግ ለኢትዮጵያ ህዘብ ጊዜው አሁን ነው!!!
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መር ሽብርተኛነት
‹‹የኦሮሚያ ህጻናት ወታደራዊ ሥልጠናው ተጠናክሮ ቀጥሏል…*…… ዐማራ የአያትህን ጡት ቆርጧል፣ ዐማራ ስታይ እንዳታልፈው ግደል፣ ሚኒልክ መሬትህን ወርሮ ይዟል፣ ለማስለቀቅ ታገል። ደሃ የሆንከው በሰፋሪ ምክንያት ነው፣ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቄስ፣ ዲያቆን መነኩሴ፣ አማኝ ስታገኝ አትለፈው። እረድ! ዐማራ ሆኖ እስላም የሆነም ስታገኝ ጨፍጭፈው፣ ለዘር እንዳታስቀር! አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም! ተብሎ የጥላቻ መርዝ እየተጋቱ ከሚያድጉ ህጻናት ከአራጅ ሌላ ምን ሊሆንላችሁ ፈልጋችሁ ኑሯል? …… በትግራዩ ጦርነት የሚማረኩ የትግሬ ህጻናት ወታደሮች ቆስለው እንኳ ህክምና እየተደረገላቸው ምግብ ሲቀርብላቸው አሻፈረኝ ይሉ እንደነበር ሰምተናል። ምክንያታቸውም በጦርነቱ ቆስላችሁ ከተማረካችሁ ” በመርዝ ” ይፈጇችኋል ተብለው ፀረ ዐማራ ሥልጠና ስለተሰጣቸው ነው። ሃኪሞች ምግብ እየቀመሱ ነው ታካሚዎቹን ሲያበሏቸው የከረሙት።
… በኦሮሚያና በትግራይ ለዘመናት የተዘራው ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ትርክት አድጎ እና ጎምርቶ፣ አሽቶም ፍሬአፍርቶ ለዚህ ደርሷል። እነ ሽመልስ አብዲሳም የዚሁ ፍሬ ውጤቶች ናቸው። ” ሸረሪቷን ገድለናታል። የሚቀረን የሸረሪቷን ድር ማጽዳት ነው” አይደል ያለው። … አንዳንዱ ምስኪን ዐማራ የኦሮሚያ ፖሊስ ሲያይ ሩጦ ‘አድነኝ ” ይለዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ምላሽም ‘ነፍጠኛ ልጠብቅ አይደለም የቆምኩት…” “ኦሮሞ ኦሮሞን አይገልም” አለ ዐቢይ አሕመድ…… በኦሮሚያም በኢትዮጵያም የምትኖሩ ዐማሮች ግን ፈጣሪ ይሁናችሁ።›› (1)
‹‹ አዲስ አበባ የምትዋጥ፣ የማትተፋ፤ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ናት!!!›› ‹‹እናቱ የሞተችበትም፣ እናቱ ወንዝ የወረደችበትም ህፃናት እኩል ያለቅሳሉ!!!›› በህገመንግሥቱ ‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ›› እየተባለ ባለበት አገር የአማራ ዜጎች እናቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና አዛውንቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ይታረዳሉ:: የምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለእነዚህ ዜጎች በህይወት የመኖር መብት ሲጮሁላቸው አልተሰማም፡፡ የታረዱት ዜጎች ጩህት በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ በትግራይ ክልል ማይካድራ፣ በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ የአማራን ንጹሃን ዜጎች የዘር ማፅዳት ጩህት ከሩቅ ይጣራል፡፡ የዘር ማፅዳቱን ዘመቻ የፌዴራል መንግሥት ብልጽግና ፓርቲ መሪነትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሽመልስ አብዲሳ ፊታውራሪነት የሚመራ መንግሥት መራሽ ሽብርተኛነት ነው፡፡ ይህ ዘረኛና ተረኛ መንግሥት መራሽ ሽብር ተኛ ድርጅት ህወሓትን ከመታ በኃላ አማራን ዘር በማረድ ቀጥሎ ለመምታትአቅዶል፡፡ኦነግን ከዳር አገር ወደ መኃል አገር አዝምቷል፡፡ የኦነግና የብልጸደግና ፓርቲ የፖለቲካ ሴራ ወንዝ አይሻገርም፡፡
የስድስተኛው ዙር የምርጫ ተሰታፊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኦሮሚያ ክልል መንግሥት መራሽ ሽብርተኛነት የኦሮሞ ጦር (ልዩ ሀይል) ከእንጦጦ ተራራ ጀርባ የሰፈረው ዘር የማጽዳት ወንጀል ለመፈፀምና የአዲስ አበባን ህዝብ አስፈራርቶ ለመግዛት የታቀደ የፖለቲካ ሴራ ነው፡፡ ለአዲስ አበቤ ህብረ ብሔር ወጣቶች ‹‹ አዲስ አበባ የምትዋጥ፣ የማትተፋ፤ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ናት!!!›› መተሃራ የስኳር ፋብሪካ የኦነግ ሸኔ የጦር ካንፕ ሠፍሮል፣ አርባ ምንጭ ነጭ ሣር ፓርክ የኦነግ ሸኔ የጦር ካንፕ ሠፍሮል ዳሩን መኃል አድርጎ ህዝቡን በኦነግ ሠራዊት ለመግዛት ብልጸግና ፓርቲ አሰፍስፎል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ናዝሬት፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ፣ አሰላ፣ ወዘተ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የህዝቡን ደህንነትና የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም እንደ ሻሸመኔ ከተማ መሠረተ-ልማቶች እንዳይወድሙ ወጣቶች ህዝቡን አስተባብረው ነቅቶ መጠበቅና ለእናት ከተማህ ሠላም ለማስከበር፣ በክብር ዘብ መቆምህ የዜግነት ክብርህ መሆኑን አትርሳ፡፡
- የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችሉት አመቺ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገልጾ፤ በገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዘንድ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ፍላጎት አለመኖሩ ከምርጫው ለመውጣቱ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል።
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፀሐፊ የሆኑት አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ “ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል” ብለዋል። ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያወጣቸው በነበሩ መግለጫዎች የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። (1)
- የባልደራስ ለእውነተኛ ፓርቲ መሪ እስክንድር ነጋ እስር ቤት እያሉ በምርጫው እንዳይካፈሉ ተደርጎል፡፡››
- በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ እና ሐረሪ ክልል ሁለት የአብን ዕጩዎችና ሦስት አባላቱ ታስረው እንደተፈቱ ጠቅሰዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ በመስቃን አካባቢ ሁለት የግል ዕጩዎች ታስረው እንደሚገኙ ገልጸዋል።
- በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል።
- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ቢያንስ በ46 (አርባ ስድስት) የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎቹን ማስመዝገብ እንዳልቻለ አስታውቆል፡፡ ‹‹ምርጫን ዴሞክራሲያዊ በማድረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ሂደቱ ትልቅ ሚና አለው፡፡ ሂደቱን ካበላሸንው ዉጤቱን ይወስነዋል፡፡ አሁን እንደምናየው ብልፅግና ኦሮሚያ ላይ ብቻውን ለመወዳደር እየሄደበት ያለው መንገድ አገርንም ጭምር ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል፡፡›› ሲሉ የፓርቲው የድርጅቱ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዋስይሁን ተስፋዬ አስጠንቅቀዋል፡፡ ኢዜማ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ባሉ የምርጫ ወረዳዎች ያቀረባቸው ዕጩዎች ከመመዝገባቸው በፊት ዛቻና ማስፈራራት ስለደረሰባቸው በፀጥታ ሁኔታ ችግር የተነሳ በተለያዩ የምርጫ ወረዳዎች ዕጩ ለማስመዝገብ አልቻለም፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የኢዜማ ዕጩዎች ከተመዘገቡ በኃላ ያለመከሰስ ሙሉ መብት እንዳላቸው እየታወቀግሞ ፣ ዕጩዎችን ማሰር፣መደብደብና የመሳሰሉት ከመንግሥት ጋር በተያያዘ የገጠሙት ችግሮችን ፓርቲው በዝርዝር አቅርቦል፡፡ በኦሮሚያ ክልል፣ የኢዜማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ በግፍ በጥይት ተገድለዋል፡፡ (3)
- ቤንሻንጉል ጉሙዝና እና በአራቱ የወለጋ ዞኖች በፀጥታ ስጋት ምክንያት ከተቀሩት የኦሮሚያ አካባቢዎች የዕጩዎች ምዝገባ ዘግይቶ የተካሄደ ሲሆን በእነዚህ አካባቢዎች አሁንም የፀጥታ ችግር ስጋት መኖሩን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
- የስድስተኛው ዙር ምርጫ በትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶል፡፡ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ፣ አሰላ፣ ለቀምት፣ ጎባ፣ አዳማ፣ ደብረዘይት፣ በተለይ በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ከተሞች ውስጥ የምርጫው ሂደት ልዩ ጥበቃ ካልተደረገ የሰዎች እልቂትና የዘር ፍጅት ሊከሰት ስለሚችል ከወዲሁ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል እንላለን፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መር ሽብርተኛነት
‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው።
በኢትዮጵያ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የዘር ማፅዳትና ኃይማኖት ፍጅት ከ1982 እስከ 2013ዓ/ም
- በ1982 ዓ/ም መግቢያ ላይ፣ ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ፣ በአሶሳ ከተማ ኦነግና ሻዕቢያ የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። በሻብያና በኦነግ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ ነበር፡፡ ሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌንጮ ለታ በጆኖሳይዱ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
- በ1984/85 ዓ/ም በአርሲ ሃገረ-ስብከት አርባጉጉ አውራጃ በ680 ካህናትና ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ አረመኔዊ ተግባር ታርደዋል፣ +ተቃጥለዋል ከገደል ላይ ተወርውረዋል፡፡ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ አርባ ሦስት ሽህ ምዕመናን ተሰደዋል፡፡
- በምዕራብ ሐረርጌ ሃገረስብከት አሰቦት ገዳምና አቡነ ሣሙኤል ገዳም መነኮሳትና ምዕመናን በግፍ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡
- 1998 ዓ/ም በህዳር 8 እና 9 ቀን፣ በአርሲ ሃገረስብከት ኮፈሌ ቆሬ ከተማ አይሻ ሰበካ ስድስት ምዕመናን ተገለዋል፡፡ ከመቶ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተከታዬች ቤታቸው ተቃጥሎ ተሰደዋል፡፡ የማርያም ቤተከርስቲያን ተቃጥላለች፡፡
- 1999 ዓ/ም ከመስከረም እስከ ጥቅምት አምስት፣ በሻሻ ዴዴሳና በሞናቶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎል፡፡ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፣ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡
- በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወንጀሎች ተፈፅመዋል፡፡
- በ2012 ዓ/ም ሃጫሉ ሁንዴሳ 187 ሰዎች ተገድለዋል የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!! በዚህ የህቡዕ መፈንቅለ መንግሥት የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የአርባ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው ለዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት (International Criminal Court) በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
- በ2013 ዓ/ም በጥቅምት 9 ቀን እና ጥቅምት 13ቀን እንዲሁም ጥቅምት 23 ቀን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት እስካሁን የ54 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ይታወሳል። የክልሉ ቃል አቀባይ ጥቃቱ የተፈጸመው በስብሰባ ስም በአንድ ቦታ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ነው ብሏል።
- ‹‹በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጉር ወረዳ ዳቢስ በሚባል ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ። “በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ መሆኑን” የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ ይህንኑ አረጋግጠዋል።…”ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ብለዋል።…
- ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ በሆሮጉድሩ ወረዳ ውስጥ አማራዎች ላይ ማንነትን መሰረት ባደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ምክንያት ከ60 በላይ ወገኖቻችን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ታርደውና ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው ለችግር ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡ ንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ሆነዋል፡፡
‹‹በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!›› ‹‹ በኃይል የመጣ፣ በኃይል ይወጣ!!!››‹‹ከምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለውና!!!›› ‹ብልፅግና ሸኔ› ኦነግ ሸኔና ኦነግ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court) መቅረባቸው አይቀርም!!! እንደ ህወሓት የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ደኢህዴን ወንጀለኞች ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአሜሪካ፣ የእንግዚዝ፣ የካናዳ፣ በአጠቃላይ የአለም ህብረተሰብ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ተከታታይ የዘር ማፅዳት ወንጀል የኦነግ፣ ኦነግ ሽኔ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ወንጀል በማስረጃ አቅርቦ ማስቀጣት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው፡፡ የዘርና የኃይማኖት ፍጅቱንና ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ የኣለም ህብረተሰብ ዓይን ኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ነው ለአንዴና ለሁሌ በነፃነት በህይወት የመኖር መብታችንን ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው!!!! አራጆቻችንን ለዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መስጠት ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን፡፡ ለስድስተኛው ዙር ምርጫ ለመታዘብ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ስለተጋበዙ ፌዴራል መንግሥት ብልፅግና ፓርቲና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ሽብርተኛነትን አጋልጦ መስጠት ጊዜው አሁን ነው!!! የኦነግ ሠራዊት በህዝብ ላይ ጥቃት ቢፈፅም የዓለም ሠላም አሰከባሪ ኃይል በኢትዮጵያ ምድር እንዲገባ ህዝብ በታረዱት ወገኖቹ ስም ይጠይቃል!!! የኦነግ ተረኞቹ አራጆች የሚወገዱት ጊዜው አሁን ነው!!! በተመሳሳይ ሁኔታም ትግራይ ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው፤በአንደኛ ደረጃ ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ ለደረሰው ጠቅላላ ጉዳት፣በሁለተኛ ደረጃ፣ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጠናቋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሰቆቃ፣በሦስተኛ ደረጃ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ በእነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የዘር ማፅዳት ወንጀል፣ የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በገለልተኛ አካል በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጣራ ማድረግ ለኢትዮጵያ ህዘብ ጊዜው አሁን ነው!!!
ምንጭ፡-
(1) ‹‹የኦሮሚያ ህጻናት ወታደራዊ ሥልጠናው ተጠናክሮ ቀጥሏል… ዘመድኩን በቀለ/ | 13/03/2021 | 0
(2) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ “ተገፍቶ መውጣቱን” ገለፀ/4 መጋቢት 2021
(3) ኢዜማ ከዕጩዎች ምዝገባ ጋር ለደረሰበት መጉላላት ቦርዱንና መንግሥትን ወቀሰ(ሪፖርተር ጋዜጣ/4/3/2021)