ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ካለፈው ክረምት ጀምሮ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግለት ቆይቶ ድጋፍ ሲደረግለት ቆይቶ ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

የቀብር ስነስርዓቱ ዛሬ 9፡00 ሰዓት ላይ በኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መቃብር ይፈጸማል፡፡

ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው በሙዚቃ ህይወቱ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ አራት ዓይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት ይችል ነበር፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ሙዚቃን የጀመረው ተወልዶ ባደገባት በድሬዳዋ ሲሆን በ1967/68 የአርፈን ቀሎ ባንድ 2ኛ ትውልድ በመባል በሚጠራው ከአዱ ቢራ ባንድ መስራቾች ከሚባሉት የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ሂሜ የሱፍ፣ አብዱ ሸኩር፣ መሀመድ ጠዊል ጋር በመሆን አንደኛው መስራች ነበር፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ የጋዜጠኝነት ህይወትን እስከሚቀላቀል የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃን በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ለማስተዋወቅ እድል አግኝቶ ተጠቅሞበታል፡፡

በ1968 ዓ.ም በሪሳ ጋዜጣ ስራ ሲጀምር ኢብራሂም ሀጂ አሊ አንዱ ጋዜጠኛ ነበር፡፡

ኢብራሂም የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንደነበርም በቅርብ የሚያውቁት እና የእሱን ስራዎች የተጫወቱ ይመሰክሩለታል፡፡

በ1987 ዓ.ም ሬዲዮ ፋና ሲመሰረት ፋናን ከተቀላቀሉት አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከልም አንዱ ሲሆን ተወዳጅ የሆነውን ፋና አፋን ኦሮሞ ፕሮግራምን አዘጋጅቶ በማቅረብም ይታወቃል፡፡
ኢብራሂም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለ ሲሆን ህይወቱ እስክታልፍ ድረስም የስፖርት ጋዜጠኛ ነበር፡፡

አፋን ኦሮሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲያድግም ጥረት ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply