You are currently viewing ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግንቦት 10/2015 ዓ/ም       አዲስ አ…

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አ…

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ “የታሰርኩት መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚተገብረውን ፖሊሲ በመተቸቴ ነው” አለች። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ጋዜጠኛ መስከረም አበራን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ጊዜ ቀጠሮ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። እነ መስከረም ዛሬ ችሎት የቀረቡት ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም በነበረው ቀጠሮ ፖሊስ “በአማራ ክልል ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር” በሚል የከፈተውን መዝገብ አቋርጦ “የሽብር ወንጀል መዝገብ” በመክፈቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱን አስመልክቶ ነው። ፖሊስ በዛሬው ቀጠሮም እነ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ላይ የሰነድ ፣ የቴክኒካልና ፎረንሲክ ማስረጃዎችን እንዲሁም የሰው ምስክሮችን በከፊል አሰባስቤያለሁ የተቀሩትን ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የእነ መስከረም ጠበቆችም ከ34—42 ቀን ድረስ በእስር በቆዩ ደንበኞቻቸው ላይ ፖሊስ ሰራሁ እያለ የሚያቀርባቸው ክንውኖች ተመሳሳይና እድገት የማያሳዩ በመሆናቸው የእነ መስከረም የዋስትና መብት ተከብሮ ከእስር እንዲወጡ መከራከራቸውን ሮሃ ቲቪ ችሎት ተገኝታ ተከታትላለች። “ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በሁከትና ብጥብጥ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ባለበት ወቅት ያሰባሰባቸውን ማስረጃዎች ነው አሁን በሽብር ወንጀል በከሰሰበት ወቅት እያቀረበ ያለው” ሲሉ ጠበቆቹ ተከራክረዋል። በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ወንጀሉ የተፈፀመው በአመራር ደረጃ ነው ማለቱን የተቃወሙት ጠበቆቹ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ አመራር የሆነ ሰው እንደሌለም ለችሎቱ አስረድተዋል። በተጨማሪም ጠበቆቹ እነ መስከረም በዋስ ቢወጡ መረጃ የማጥፋትም ሆነ ፣ ከአገር የመውጣት እድል ስለሌላቸው ዋስትናቸው እንዲጠበቅ ችሎቱን ጠይቀዋል። በችሎቱ የተናገረችው መስከረም አበራ በበኩሏ “የታሰርኩት በፖለቲካ ምክንያት ነው፣ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ፖሊሲ በሚዲያ በመተቸቴ ነው የታሰርኩት፣ ሌላ ወንጀል አልሰራሁም” ብላለች። “የአማራ ህዝብ መብቱን ለማስከበር ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፀጥታ አካላት ጥይት በመተኮሳቸው ለተነሳው አመፅ እኔ ተጠያቂ አይደለሁም “ስትልም አክላለች። የግራ ቀኙን ያደመጠው ችሎቱም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ አርብ ግንቦት 11/2015 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል። ሮሃ ሚዲያ እንደዘገቡ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply