
ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ የ The International Women of Courage Award Awardee!!! ከሽልማቱ በኋላ ማዕዛ መሀመድ የተናገረችው.. “…ድርሻህ ነው ተብሎ የተሰጠውን ክልል ጨምሮ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ማህፀናቸው ተቀዶ ፅንሳቸው ለሚጣለውና በጅምላ ተጨፍጭፈው በዶዘር ለሚቀበሩት አማራ እናቶቼና እህቶቼ ብዙም ትርጉም ባይኖረውም ጉዳያቸውን የዓለም መሪዎች ፊት አድርሰናል። የዓለም መሪዎች ሌት ከቀን ለሚምሉበት ለሰብዓዊነት መርህ ዋጋ ሰጥተው ይህ ሁሉ ግፍ ከሚፈፀምበት አማራ ጎን ይቆማሉ ወይስ ዲፕሎማሲያቸው እንዳይበላሽባቸው ከገዥው ኦህዴድና ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጎን ይቆማሉ? የሚለውን ወደ ፊት እናየዋለን።” ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አክብሮቴን ለመግልፅ ቃላት የለኝም። እግዚአብሔር ያክብርልኝ። ትግሉ ይቀጥላል! አሚማ እንደዘገበው
Source: Link to the Post