ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ እና ራውዳ አዲስ “እውቀት ነጻ ያወጣል” በሚል መሪ ኃሳብ ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰቧቸውን በርካታ መፅሀፍት ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁ

ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ እና ራውዳ አዲስ “እውቀት ነጻ ያወጣል” በሚል መሪ ኃሳብ ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰቧቸውን በርካታ መፅሀፍት ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስረከቡ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ እና ራውዳ አዲስ “እውቀት ነጻ ያወጣል” በሚል መሪ ኃሳብ ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰቧቸውን በርካታ መፅሀፍት ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስረክበዋል።

ከበጎ ፈቃደኞች ያሰባሰቧቸውን ሁለገብ መፅሀፍት ወደ ሁመራ ጭኖ ያቀናው የዘመቻው አስተባባሪ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ለአቶ የአብስራ እሸቴ እና በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በመታገላቸው እስከ አዲስ አበባ ድረስ በእስር ዋጋ ለከፈሉት ለአቶ ነጋ ባንቲሁን አስረክቧል።

በርክክቡ ወቅትም ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ ላለፉት 30 ዓመታት በትሕነግ አገዛዝ ምክንያት የአማርኛ ቋንቋ ተገድቦ በቆየበት የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ለስነ ጽሁፍ እድገት የሚረዱ በርካታ መፅሀፍት የተካተቱበት መሆናቸውን ገልጧል።

በሁመራ ቤተ መፅሀፍት ተገኝተው የተሰበሰቡ መፅሀፍትን ከጋዜጠኛ በለጠ ካሳ እጅ የተረከቡት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪው አቶ የአብስራም በዚህ በጎ ተግባር ለተሳተፉት ወገኖች ምስጋና አቅርበዋል።

“እውቀት ነጻ ያወጣ” በሚል መነሻ ኃሳብ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ፈሰስ ላደረጉ ወገኖች ምስጋና ያቀረቡት አቶ የአብስራ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲደርስበት የነበረውን በደል አውስተዋል።

ይህን በኃይልና በፖለቲካ ውሳኔ ተይዘው በቆዩ የወልቃይት ጠገዴን አማራዊ ማንነትን ለማስመለስ ማህበረሰቡ አቅሙ በፈቀደ መጠን የትጥቅ ትግል ከማድረጉ በተጨማሪም በሰላማዊ መንገድም ሲታገል መቆየቱን ተናግረዋል።

በትሕነግ በተያዙ አካባቢዎች ባሉ ት/ቤቶች ከአቶ መለስ ዜናዊ እና ከአቶ በረከት ስምኦን አብዮታዊ ድስኩር መፅሀፍት ውጭ ሌሎች በአማርኛ የተጻፉ ብዙ መፅሀፍት እንደማይገኙ ገልጸዋል።

የተበረከቱት መፅሀፍት ህጻናት የአማርኛ ቋንቋቸውን ከማሳደግ ባሻገር፣ የነበረውን የግፍ አገዛዝ የሚያጋልጡና ታሪክን የሚዘግቡ እንዲሁም የዘመኑን ቴክኖሎጅ እንዲቋደሱ እድል የሚሰጡ ናቸው ብለዋል።

በወልቃይት ጠገዴ በአማራ ማንነት ትግል የድርሻቸውን ካበረከቱትና አዲስ አበባ ድረስ በትሕነግ አፋኞች በእስር የተንገላቱት አቶ ነጋ ባንቲሁንም በርክክቡ ወቅት ተገኝተው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል።

በአማርኛ የተጻፉ መፅሀፍት ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆኑ የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ ቃል የገቡት አቶ ነጋ ጉዳዩን ሁሉም ሰው እንዲገነዘበው እናደርጋለን ብለዋል።

አቶ በለጠ ካሳ ቀደም ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ አገልግሏል፤ በተጨማሪም በአስራት ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ሲሰራ መቆየቱም ይታወቃል።

አሁን ላይ ደግሞ ከበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ባሻገር በኢትዮ ሚዲያ ውስጥ ከባልደረባው በላይ ማናዬ ጋር ሆነው ለተጎጅዎች ድምፅ በመሆን እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ የሁሉንም ድጋፍ የሚሹ ባለሙያዎች ናቸው።

ምንጭ_ኢትዮ ኒውስ ያጋራው ቪዲዮ


Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply