ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ተፈቀደ

ማክሰኞ ኀዳር 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ተፈቀደ።

ዋስትናውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በሦስት ተደራራቢ ክሶች ዋስትና አያስከለክልም በማለት የ100 ሺሕ ብር ዋስትና ፈቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ዋስትና አግዶት እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም ይህንኑ የ100 ሺሕ ብር በመቀነስ በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንደለቀቅ በዛሬው ዕለት መፍቀዱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

The post ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ተፈቀደ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply