You are currently viewing ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ሦስት ክሶች መካከል በሁለቱ ፍርድ ቤት በነጻ እንዳሰናበተው ተገለጸ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 11ቀን 2015 ዓ.ም         አዲስ አበ…

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ሦስት ክሶች መካከል በሁለቱ ፍርድ ቤት በነጻ እንዳሰናበተው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበ…

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ሦስት ክሶች መካከል በሁለቱ ፍርድ ቤት በነጻ እንዳሰናበተው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዐቃቤ ሕግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳላኝ ላይ አቅርቦት የነበረው ሦስት የተለያዩ ክሶችን በተደራራቢነት ሲሆን፣ 1ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 336(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ፤ 2ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 337(1) ፤ 3ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የሚል ነው። ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች በዋለው ችሎት ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሠሰበት 1ኛ እና 2ተኛ ክሶች በአብላጫ ድምጽ ፍርድ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በነጻ አሰናብቶታል። በሦስተኛው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) ስር የተመለከተውን ፤ በአዎጅ ቁጥር 1238/2013 የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ክሱ ተቀይሮ በጥላቻ ንግግረና በሐሰተኛ መረጃ ስርጨትን ለመከለከልና ለመቆጣጣር በወጣ አዎጅ መሰረት እንዲከለከል ብይን ተሰጥቷል። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የመከላከያ መልስ ለመሠማት ችሎቱ ለህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለዋዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ጋዜጠኛ ይድነቃቸው ከበደ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply