ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተ

በሃሚድ አወል

የ“ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰበት የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወንጀል በነጻ ተሰናበተ። ጋዜጠኛው በነጻ የተሰናበተበትን ፍርድ የሰጠው፤  ዛሬ ረቡዕ የካቲት 29፤ 2015 የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው። 

የችሎቱን ፍርድ በንባብ ያሰሙት የግራ ዳኛ “ተከሳሹ የቀረበበትን ወንጀል በመከላከሉ በነጻ ሊሰናበት ይገባል በማለት በሙሉ ድምጽ ፍርድ ሰጥተናል” ብለዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ተከስሶበት የነበረው የወንጀል ተግባር “መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት የወንጀል ተግባር” ፈፅሟል የሚል ነበር። 

ነገር ግን ችሎቱ ባለፈው ጥቅምት ወር ድንጋጌውን በመቀየር “የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር” በወጣው አዋጅ እንዲከላከል ወስኗል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

The post ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply