
ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ በፌደራል ታሰረ፤ አድራሻው በትክክል አለመታወቁ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አራጋው ሲሳይ ጋዜጠኛ ነው፤ የወሎ ቤተአምሓራ በጎ አድራጎት ድርጅት ምክትል ሰብሳቢ ፣ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር መሬት ላይ ወርዶ ቤታቸዉ ድረስ በመግባት ችግራቸዉን ስቃያቸዉት በማህበራዊ ሚዲያ ለአለም ህዝብ በማሳየት የጋዜጠኝነት ሙያዉን በአግባቡ ተወጥቷል። በበጎ አድራጎቱም በድርጅቱ የሚጣልበትን ሀላፊነት ከጓደኞቹ ጋር በዛ ጦርነት መሃል በረሃብ ለሚሰቃዩ ህዝቦች የሚችሉትን አድርጓል። ለዚህ አገልግሎት ሽልማት ቀርቶ እስር ሆኗል ! ጋዜጠኛን በማሰር ድምፅን ማፈን አትችሉም! አራጋው ሲሳይ መጋቢት 17/2015 ጠዋት ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ አካባቢ ከመኖሪያ ቤቱ የፌደራል ልብስ የለበሱ ሰዎች ወዴት እንኳን እንደሚውስዱት ሳይናገሩ ወስደዉታል። ልጅ ፍስኃ መለሠ እንዳጋራው።
Source: Link to the Post