
ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ፍ/ቤት ቀርበው ለሚያዝያ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ መጋቢት 19/2015 ረፋድ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለሚያዝያ 2/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧቸዋል። ፌደራል ፖሊስ ህገ ወጥ አደረጃጀት በመመስረት፣ ወጣቶችን በየቦታው በማደራጀት የሚል ክስ በማቅረብ ለምርመራ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍ/ቤቱን ጠይቋል። ለሁለቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ የሆነው አዲሱ አልጋው ቀርቦ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ተከራክሯል። ግራ ቀኙን ያዳመጠው ፍ/ቤቱም 13 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሚያዝያ 2/2015 እንዲቀርቡ አዟል። ጋዜጠኞቹ ሜክሲኮ ከተያዙበት መጋቢት 17/2015 ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው ይገኛሉ። ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ከቤቱ የተወሰዱትን የአማራ ድምጽ ሚዲያ ኮሚፒተሮችን ፓስ ወርድ ክፈት በሚል ስለመጠየቁ ተሰምቷል።
Source: Link to the Post