You are currently viewing ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ የክስ ጉዳያቸውን እንዲያዩ የተሰየሙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዳኛ እንዲነሱላቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም…

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ የክስ ጉዳያቸውን እንዲያዩ የተሰየሙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዳኛ እንዲነሱላቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም…

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ የክስ ጉዳያቸውን እንዲያዩ የተሰየሙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዳኛ እንዲነሱላቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ፀረ-ሽብር ወንጀል ችሎት በጻፉት ደብዳቤ የክስ ጉዳያቸውን እንዲያዩ የተሰየሙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዳኛ እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል። ታዲዎስ ታንቱ ያቀረቡት አቤቱታ የሚከተለው ነው:_ የተሰየሙ ዳኛ እንዲነሱልኝ ለመጠየቅ የቀረበ አቤቱታ በከሣሽ የፈ/ጠ ዐ/ሕግና በተከሣሽ በእኔ መካከል ባለው የወንጀል ክስ የክሱ ሂደት በዚህ ችሎት እየተመራ እስካሁን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ችሎቱን ይመሩት የነበሩት ዳኞች ወደሌላ ችሎት መዛወራቸውን ተከትሎ ሌሎች ክብራን ዳኞች ከጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መመደባችሁን ተከሳሽ ልረዳ ችያለሁ። 1. ተከሣሽ የተከሰስኩት በዋናነት የኦሮሞ ብሔረሰብን እና ባለሥልጣናትን ተሳድበሃል፤ ህዝብ ብጥብጥ እንዲያነሳ አድርገሃል፤ ተብዬ ከመሆኑም በላይ ቀደም ሲል በዚህ ችሎትም ይህን በጠቅላይ ፍ/ቤት በዋስትና ጉዳይ ላይ በዋስ እንድፈታ ክርክር በሚቀርብበት ጊዜ በ15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ዋስ እንድለቅቅ ትእዛዝ ሲሰጥ:_ 1) በድምፅ ልዩነት ሊፈታ አይገባም ሲሉ በሀሳብ ልዩነት ትእዛዝ ያሠፈሩት ክቡር ዳኛ የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ በመሆናቸው እንዲሁም፣ 2) በጠቅላይ ፍ/ቤት በድምጽ ልዩነት የዋስትና መብቴ ቀሪ እንዲሆን በአብላጫ ድምጽ ውሣኔ የሰጡት ክቡራን ዳኞች የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች በመሆናቸው፣ 3) በተጨማሪም ችሎቱ ክሱን እንድከላከል ብይን ሲሰጥ ከመከላከያ ሚኒስትር ብ/ጄ መሸሻ አረዳ ሒርጳ የተባሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የፃፉትን የግል አስተያየት እንደባለሙያ አስተያየት ተቀብሎ በመውሠድ እንድከላከል ብይን ሲሰጥ ችሎቱ በገለልተኛ አይቶ ይወሥንልኛል የሚል እምነት እንዳይኖረኝ አድርጎኛል። 4) እንዲሁም ይህ ችሎት እየተመራ ያለው የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ በሆኑት ክቡር ዳኛ የኦሮሞ ተወላጅ በመሆናቸው ይህ ደግሞ ተከሽ ከተከሰስኩበት የክስ ዝርዝር አንጻር በገለልተኛነት ፍትሐዊ ውሣኔ እገኛለሁ ብዬ በግል እምነት ሥለሌኝ በግሌ ይህን አቤቱታ ለማቅረብ ተገድጃለሁ፡፡ በመሆኑም የተከበረው ፍ/ቤት በተከሰስኩበት ጉዳይ ፍትሐዊ የሆነ ውሣኔ ለማግኘት አንድችል ጉዳዩ ወደ ሌላ ችሎት እንዲዛወርልኝ ወይም የችሎቱ ሠብሳቢው ዳኛ ማለትም ክቡር ዳኛ ረቡማ ተፈራ በሌላ ሰብሳቢ ዳኛ እንዲተኩልኝ በትህትና አመለክታለሁ፡፡ አመልካች ተከሣሽ ታዲዎስ ታንቱ፣ ደብዳቤው_በሮሃ ሚዲያ ገጽ የተጋራ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply