ጋዜጠኛ እና ፕሮግራም አቅራቢ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ነበር::ተወዳጁ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/rl32ShEazEh2ndRRomNCcOkkAjhdDBpOmp2eojwPmt3wMytRVf009AqYgSiCDzVgXSbZ3DBDQrqybaIv3VkLrHXcbPCGSj340GRLd313Np7CFOL6jcSh2N6aM2lUrpaimo1McTNYZ2hRFhghukhInmrUYVdvcEXPOceS-e1udAt4DFBa_EJRO6u76w1kpzy2Gz3M77lDwrCm90nSeElpAuIyb1kNyWNrebCDrw9EDwtFfYt_G0_E9I81_xemCrUxtdmCbNfEsNawMeNY7JXZAu6FntN5WStGCX7RMa-De1KYo9SlUFYgSh5Itki-0NBjsdcct6cTf-ywlFmSlytbIw.jpg

ጋዜጠኛ እና ፕሮግራም አቅራቢ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ነበር::

ተወዳጁ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ በኤፍኤም አዲስ 97.1 “አይሬ” በተባለ የሙዚቃ ፕሮግራሙ ይታወቅ ነበር።

በኢቢኤስ ቴሌቪዥንም “ኑሮ በአሜሪካ” በተሰኘ ፕሮግራሙ ተወዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በህመም አልጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ በቴሌቪዥን ጣቢያው በፕሮግራም አቅራቢነት ሲያገለግል ቆይቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለቤተሰቦቹ ፣ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል

Source: Link to the Post

Leave a Reply