You are currently viewing ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመዘገቡ የሽብር ክስ ቀረበበት!  የአማራ ሚዲያ ማእከል   መስከረም 3 2015 ዓ/ም…

ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመዘገቡ የሽብር ክስ ቀረበበት! የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 3 2015 ዓ/ም…

ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመዘገቡ የሽብር ክስ ቀረበበት! የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 3 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጵያ ጳጉሜ 5 ቀን በፖሊስ የታፈነው የአማራ ሚዲያ ማእከል ጋዜጠኛ የሆነው ዓባይ ዘውዱ በትናንትናው ዕለት መስከረም 2 ቀን ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹በሽብር› ክስ ተመሰረተበት። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ የአማራ ተወላጆች በግፍ ተገድለዋል በማለት ለዓለም አቀፍ ተቋማት ፎቶ ግራፍ በማሰባሰብ እና በመላክ መንግስት ላይ ጫና ፈጥሯል በሚል የክስ መዝገብ ተከፍቶበታል። ሙሉ የክስ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው ጉዳዩ፡ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ስለመጠየቅ ይሆናል፡ ዓባይ ዘዉዱ ደመቀ በተጠረጠረበት የሽብር ወንጀል ድርጊት ጉዳይ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የአማራ ብሔር ተዎላጆች በግፍ ተገድለዋል በማለት ፎቶ ግራፍ በማሰባሰብ ለዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች በመስጠት በመንግስት ላይ ጫና እንዲፈጠር በማሰብ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጭ እንዲሁም አማራ ተጨቁኗል በሚል ሽፋን የአማራ ተማሪዎችን እና ማህበራትን ለዓመጽ በማደራጀት ህገ መንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሌሎች ካልተያዙ ግበረ አበሮች ጋር በመሆን ቅስቀሳ በማድረግ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ እያለ ከቀን 05/13/2014 ዓ/ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውሎ በምርመራ ቢሯችን በእስር ላይ ይገኛል። ስለሆነም የምርመራ ስራችንን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በተገቢ ሁኔታ ለማጣራት እንድንችል በወ/መ/ህ/ስ/ስ/59/1 መሰረት የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድ እንጠይቃለን። የቀረበበት ክስ ከላይ እንደሰፈረው ሲሆን ፖሊስ ባቀረበው የምርመራ ማጣሪያ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ መስከረም 5 ልደታ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል። በጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ ጋር የቀረበው ክስ እጅግ አሳፋሪ እና የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመንግስት እንደሚደገፍ ማሳያ ነው። የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአሁኑ ሰዓት ሁሉም የሚያውቀው መራራ ሀቅ ሆኖ ሳለ ጋዜጠኛ ዓባይ በብሄራቸው ብቻ በግፍ እየተገደሉ ሰላሉ አማራ ወገኖቻችን ግፍ በመዘገቡ ብቻ በገዥው በብልጽግና ስርዓት ሽብር በመፍጠር ወንጀል አስከሦታል። የአማራ ተወላጆችን እየመረጡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በምእራብ እና ምስራቅ ሸዋ እንዲሁም በቤንሻንጉል የተለያዩ ቦታዎች እየተፈጸመ ያለውን የአማራ ዘር ማጥፋትን በተመለከተ እስካሁን ጨፍጫፊዎች ላይ ለይስሙላም ቢሆን እንኳን አንድም ሰው ለፍርድ ባልቀረበበት ሁኔታ ለምን ተዘገበ ፡ ለምን ፎቷቸው ለዓለም አቀፍ ተቋማት ተሰጠ በሚል ክስ ማቅረቡ የብልጽግናን መንግስት ለአማራ ጭፍጨፋ ያለውን ይሁንታ የሚያሳይ ነው። ሌሎች ዝርዝሮችን አቆይተን ባለፈው አመት በአንድ አዳር ብቻ ከ2000 በላይ አማራዎች ተጨፍጨፈው ማደራቸው ይታወቃል። በብልጽግና መንግስት በመንግስት በመረጃ በስንቅ እና ትጥቅ የሚደገፉ መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራቸው ታጣቂዎች አልቀዋል፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸሙት አንድም ለፍርድ ሳይቀርቡ ይሄንን አሰቃቂ እና አሳዛኝ ጭፍጨፋ የዘገበው ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ ጋር ውንጀላ መቅረቡ እጅግ አሳፋሪ ነው። ዓባይ ዘዉዱ ላይ ከቀረበው የውንጀላ ክስ ሌላ የሚያሳየው ነገር ‹ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመናድ ተንቀሳቅሷል› የተባለበት አውድ ሲሆን ይሄም አማራው እየተለየ እንዲጠቃ ያደረገው ይህ ጸረ አማራ በሆነው ህገመንግስት መሰረት መሆኑን ያሳያል። የአማራን ጭፍጨፋ ሲፈጸም ምንም የማይሆነው ‹ህገ መንግስት› ጭፍጨፋው ሲጋለጥ ግን እንደሚናድ ክሱ ያሳያል። በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ዓባይ ላይ የቀረበው የውንጀላ ክስ ለአማራ ዘር ማጥፋት ድምጽ በመሆኑ እና የሚመለከተው የመንግስት አካል ጭፍጨፋውን ከማስቆም ይልቅ ዘጋቢዎችን በማፈን ስራ ላይ መጠመዱን ያሳያል። የአማራ ሚዲያ ማእከል ቦርድ ጋዜጠኛ ዓባይ እስከዛሬ በሰራው ዘገባ እና ለወገኖቹ በመቆሙ ያለውን አድናቆት እየገለጸ የአማራ ጭፍጨፋ የሚገዳቸው ሁሉ ከጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉድ ጎን እንድትቆሙ ጥሪውን አስተላፏል። እንዲህ ዓይነት ክስ የአማራው ጭፍጨፋ መቆሚያ እንዳማይኖረው ማሳየ በመሆኑ ለአማራ ህዝብ ድምጽ መሆናችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል አመላካች መሆኑን እንረዳለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply