You are currently viewing ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዐቃቢ ህግ ባቀረበበት የዋስትና ይግባኝ ጉዳይ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቦ ለጥቅምት 22/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 11…

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዐቃቢ ህግ ባቀረበበት የዋስትና ይግባኝ ጉዳይ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቦ ለጥቅምት 22/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11…

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዐቃቢ ህግ ባቀረበበት የዋስትና ይግባኝ ጉዳይ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቦ ለጥቅምት 22/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጥቅምት 11/2015 ረፋድ ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀርቦ ነበር። ቀደም ሲል ዐቃቢ ህግ በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተፈቀደለት የዋስትና መብት አግባብ አይደለም፤ ሊሻር ይገባዋል በሚል ያቀረበው ይግባኝ በችሎቱ ተቀባይነት አግኝቶ የስር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ እና ክርክር እንዲደረግበት ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም የጋዜጠኛ ጎበዜ ጠበቆች የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ20 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ሲል የፈቀደው የዋስትና መብቱ ሊከለከል አይገነኘባም በሚል በማብራሪያ የተደገፈ ምላሻቸውን ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበዋል። ጠቅላይ ፍ/ቤቱም ጥቅምት 11/2015 በዋለው ችሎት በዐቃቢ ህግ የቀረበለትን የይግባኝ ጉዳይ እና ከጠበቆቦች የተሰጠውን ምላሽ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በሚል ለጥቅምት 22/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ከጠበቃ አዲሱ ጌታነህ እና ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ በተጨማሪ ቀደም ሲል ይግባኝ አያስቀርብም በሚል እያንዳንዳቸው በአስር አስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ ችሎቱን ታድመዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply