You are currently viewing “ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት መፈረጅ የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት የለውም!” አቶ-ያሬድ ኃይለ ማርያም_የሰብአዊ መብት ተሟጋች የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)…    ግንቦት 1/2015 ዓ/ም…

“ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት መፈረጅ የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት የለውም!” አቶ-ያሬድ ኃይለ ማርያም_የሰብአዊ መብት ተሟጋች የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ግንቦት 1/2015 ዓ/ም…

“ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት መፈረጅ የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት የለውም!” አቶ-ያሬድ ኃይለ ማርያም_የሰብአዊ መብት ተሟጋች የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ግንቦት 1/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ያለአግባቡ በግፍ የታሰሩ እና ሽብርተኛ ተደርገው የተጠረጠሩ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲፈቱና ፍትህ እንዲያገኙ አበክረን እንጠይቃለን!!! የመንግስትን ፖሊሲዎች፣ እርምጃዎች እና የሥራ አፈጻጸሞች መንቀፍና መተቸት፤ እንዲሁም ባለሥልጣናትንም ማብጠልጠል ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ ማዕቀፍ ውስጥ የሚወድቁና በሕግ የተፈቀዱ ተግባራት ናቸው። ይሁንና የጥላቻም ሆነ የሃሰት መረጃዎችን ባሰራጩ ጊዜ በሚዲያ ሕጉና በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እንጂ በሽብር ሊጠየቁ አይገባም። ጋዜጠኝነት ሽብርተኝነት አይደለም። ሁሉም ጋዜጠኞች ሊፈቱ፣ ጉዳያቸውም አግባብነት ባለው ሕግ ሊታይ እና ፍትህ ሊያገኙ ይገባል። ከ10 ዓመት በፊት ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ፈርጃ ታዋክብ፣ ታሳድድና ታስር የነበረች አገር ዛሬም ተመልሳ እዛ አረንቋ ውስጥ መውደቋ ግን ያሳዝናል። ይህ ጉዳይ ቶሎ እንዲስተካከል መንግስትን ማሳሰብ ግድ ይላል። በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ይፈቱ! ጋዜጠኝነትና ለመብት መሟገት ሽብርተኛ አያስብልም! ፍትሕ በግፍ ለታሰሩ ጋዜጠኞች!!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply