ጋዜጣዊ መግለጫ

ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

የብርሃን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ግሩም ፀጋዬ ሀሙስ ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በፃፉት ደብዳቤ በግል ምክንያት ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቅርበዋል። ይህንንም ተከትሎ የባንኩ ቦርድ ጥያቄያቸውን የተቀበለ ሲሆን በባንኩ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ምንም ዓይነት ክፍተት እንዳይፈጠር በምትካቸው የኦፕሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሰለሞን አሰፋን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ  ለወደፊት ባንኩን በቋሚነት የሚመሩትን ፕሬዝዳንት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያሳውቅ ሲሆን፤ የባንኩን አመታዊ አፈጻጸምና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሚያካሂደው ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ እንዲሁም በባንኩ ማህበራዊ ድህረ-ገፅ ላይ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የብርሃን ባንክ አ.ማ. ዳይሬክተሮች ቦርድ

The post ጋዜጣዊ መግለጫ appeared first on Capital Newspaper .

Source: Link to the Post

Leave a Reply