ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሃት ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ መግባታቸው ተገለፀ። አማራ…

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሃት ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ መግባታቸው ተገለፀ። አማራ…

ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሃት ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ መግባታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ትሕነግ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር በታጣቂዎቹ በኩል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል። ፅንፈኛው ቡድን የመንገድ መሰረተ ልማት በሌለበት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ከ40 በላይ የመንግስት እና በርካታ የግል ተሽከርካሪዎችን ይዞ ለመደበቅ ያደረገው ሙከራም መክሸፉን ነው ኮሎኔል ደጀኔ የተናገሩት። ተሽከርካሪዎቹን ከፅንፈኛው ቡድን ሀይሎች አስጥሎ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰራዊቱ ባደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ መታወቂያ እና ፓስፖርቶች ተገኝተዋል። የተለያዩ ሰነዶቻቸውን ጥለው ከሸሹት መካከል የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት ፣ የማይጨው አስተዳዳሪ የነበረው ሀፍቱ ኪሮስ እና ሌሎች የወረዳ አመራር የነበሩ ሰዎች ሰነድ ይገኝበታል። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት ጌታቸው ረዳ በዴላ በኩል ከሸሸው ቡድን ውስጥ እንደሚገኝበትም ነው ኮሎኔል ፀጋዬ የገለጹት፡፡ በመከላከያ ሰራዊቱ ከተያዙት ተሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ በአሻራ የሚከፈቱ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ አራቱ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራ ከፌደራል መንግስቱ ለትግራይ ክልል የተበረከቱ አምቡላንሶች ይገኙበታል። ፅንፈኛው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና ቦቴዎችንም ሰራዊቱ ወደ ማይጨው ከተማ እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል። ዘገባው የኤፍቢሲ ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply