ጌታቸው ረዳ ”ክው” ብሏል።በትግሪኛ የሰጠው መግለጫ።ምን ይዟል?

ጌታቸው ረዳ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ =========ጉዳያችን ምጥን =========ጌታቸው ረዳ በትግርኛ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል። ጋዜጠኞቹ ይችን ምሽት ጌታቸው አጠገብ መቀመጥ እንዳስጨነቃቸው ከጠያቂዎቹ መርበትበት ለመረዳት የስነ ልቦና ጠቢብ መሆን አይጠይቅም። ቢጨነቁም ምክንያት አላቸው። የህወሃት ባለስልጣናት ባሉበት ሁሉ እያነፈነፈች ድንገት የምትመጣው ድሮን በእዚህ ምሽት አትመጣም ብለው እንዴት አይፈሩም? ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ወደ ጌታቸው የተደበቀበት ኮንቴይነር የተላኩት ጋዜጠኞች አንተ ሂድ አንተ ሂድ ሳይባባሉ አይቀሩም። ጌታቸውም ተጨንቋል።ራሱን ሳይበላው የግራ እጅ ጣቶቹን ወደ ጸጉሩ ጋር ይልክና መልሶ ያወርደዋል። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply